ዜና

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳትን ለወጪ ገበያ በባቡር ማጓጓዝ ጀመረች

ኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ወደ ጅቡቲ በባቡር ለመጀመሪያ ጊዜ ማጓጓዝ ጀመረች ከዚህ በፊት ወደ ሀገር ዉስጥ ገቢ ምርቶችን ለማስገባት ብቻ ያገለገል የነበረዉ የአዳማ - ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የቁም እንስሳትን ማጓጓዝ ጀምሯል። የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ እንደገለፁት በአዳማ በኩል የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርትን ወደ ውጭ ሀገራት ጥራት ያለውን የስጋ ምርት የመላክ አቅምን ከመጨመሩም ባሻገር የትራንስፖርት መጨናነቅን ይቀንሳል። ከአዳማ ወደ ጅቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መሆኑን ያስታወቁት ስራ አስፈፃሚው ይህን አገልግሎት በመጀመራችን አቅማችን ከፍ ያደርገዋል ብለዋል። በባቡር ትራንስፖርት በመጠቀም ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከው የእንስሳት ንግድ የህገወጥ ንግድ እንቅስቀሴንን ከማስቀረቱ ባለፈ ጊዜ…
Read More
የድቪ 2026 ማመልከቻ ከአንድ ሳምንት በኋላ ይጀመራል

የድቪ 2026 ማመልከቻ ከአንድ ሳምንት በኋላ ይጀመራል

የዓለማችን ልዕለ ሀያል የሆነችው አሜሪካ ከፈረንጆቹ 1995 ዓመት ጀምሮ በድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ በመውሰድ ለይ ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ ለዚህ እድል ከተፈቀደላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በየዓመቱ በአማካኝ ከ4 ሺህ እስከ 5 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ ያቀናሉ፡፡ የድቪ 2024 እድለኛ ኢትዮጵያዊን የቪዛ ማመልከቻቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ የሚያበቃ ሲሆን የድቪ 2025 እድለኞች ደግሞ ከያዝነው መስከረም ወር መጠናቀቅ በኋላ ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የቪዛ ጥያቄያቸውን ማቅረብ ይጀምራሉ፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም የድቪ 2026 የማመልከቻ ጊዜ ከአንድ ሳምንት በኋላ የሚጀመር ሲሆን ለአንድ ወር እንደሚቆይ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታውቋል፡፡ የማመልከቻ ጊዜው ከመስከረም 21 ቀን እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት 30 ቀናት ይቆያል የተባለ ሲሆን…
Read More
የኤርትራ ሰራዊት ተጨማሪ ቦታዎችን እየያዘ ነው መባሉን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ

የኤርትራ ሰራዊት ተጨማሪ ቦታዎችን እየያዘ ነው መባሉን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባበለ

የኤርትራ ሰራዊት ቀደም ሲል ከያዛቸው አካባቢዎች ውጭ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው መባሉን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስተባብሏል፡፡ የኤርትራ ሰራዊት ከጦርነቱ ወዲህ የያዛቸውን አካባቢዎች በማስፋፋት ከአዲግራት ከተማ በቅርብ ርቀት በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል መባሉን ያስተባበሉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እኔ እስከማውቀው ድረስ የኤርትራ ሰራዊት ከነበረበት አልወጣም አዲስ የያዘውም መሬት ይለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሰራዊቱ ቀደም ሲልም ከነበረበት የዛላምበሳ አካባቢ እንዳልወጣ የገለጹት አቶ ጌታቸው እስካሁን ባለኝ መረጃ ወደ አዲግራትም ሆነ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ያደረገው አዲስ እንቅስቃሴ የለም ሲሉ ጥያቄውን አጣጥለዋል፡፡ በኤርትራ ሰራዊት የተያዘው አካባቢ የኢትዮጵያ መሬት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ጉዳዩን የመከታተል ኃላፊነት መሆን የነበረበት የፌዴራሉ መንግስት እንደሆነ በማስታወስም፤ ሆኖም መንግስት በአካባቢው…
Read More
ኢትዮጵያ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ኢትዮጵያ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት ለመዋዕለ ህጻናት ወይም ኬጂ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዳይማሩ ከልክላ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኬጂ ተማሪዎች እንዳይማሩ አግዶት የነበረውን እንግሊዘኛ ቋንቋ በድጋሚ እንዲሰጥ መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ቢሮው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ክልከላ የጣለው ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ በሚል እንደነበር በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቅድመ መደበኛ (ኬጂ) የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በዚህ ሳምንት በተጀመረው የ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በሳምንት ለአምስት ጊዜ እንደሚሰጥ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ያዘጋጀው የእንግሊዘኛ ቋንቋ የተማሪዎች መፅሐፍ እና የመምህራን መምሪያ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች ተሰራጭቷል። ሕጻናት ወደ አንደኛ ክፍል ከመሸጋገራቸው አስቀድሞ ባለው ቅድመ መደበኛ ደረጃ ለሚማሩ…
Read More
በአማራ ክልል ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልተመለሱም ተባለ

በአማራ ክልል ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት አልተመለሱም ተባለ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እንዳስታወቀው በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ልውውጥ የሚስተዋልበት አማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዘገብ አቅዶ ነበር፡፡ ይሁንና ከነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ተማሪዎች 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ " ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 292 ሺሕ በላይ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 1.2 ሚሊዮን በላይ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ 180 ሺሕ ተማሪዎች ተመዝግበዋል " ብሏል፡፡ " በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባው እየተካሄደ ነው፡፡ ትንሽ እሱ ላይ መዘግየት ይታያል፡፡ እስካሁን በጠቅላላ ወደ 1.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው የተመዘገቡት የእቅዱን ወደ 24 ፐርሰንት…
Read More
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ለማድረግ ወሰነ

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ለማድረግ ወሰነ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ እንዲካሄድ መወሰኑ ይፋ ተደርጓል። ጉባዔው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ላይ ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ በተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ መቀየሩን የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ጉባኤው አዲስ አበባ ላይ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርቦ በካፍ ተቀባይነት ማግኘቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል። በዚህም መሰረት የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በቀጣይ ጥቅምት ወር በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል። ካፍ ዛሬ በሰጠው የቅድመ ጠቅላላ ጉባኤ ጋዜጣዊ መግለጫ የ2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው የካቲት ወር በናይሮቢ ፣ ካምፓላ እና ዳሬ ሰላም እንደሚካሄድ አሳውቋል። የ2024 ቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጥቅምት እና…
Read More
በአዲስ አበባ የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ማዕከል ሊማቋቋም ነው

በአዲስ አበባ የጉበት ንቅለ ተከላ ህክምና ማዕከል ሊማቋቋም ነው

በኢትዮጵያ የጉበት ንቅለ ተከላ ፕሮግራም በትብብር ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ በጤና ሚኒስቴር እና በካሊፎርኒያ ፓሲፊክ የሕክምና ማዕከል መካከል ተፈርሟል። ይህ ተነሳሽነት በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ቅድስት ኪዳኔ ይማም የሚመራ ሲሆን በሰሜን ካሊፎርኒያ ያሉ ባልደረቦቻቸውን በማስተባበር ወደ ተግባር የተቀየረ ነው። ከዚህ ቀደም ዶ/ር ቅድስት አገልግሎቱን በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል የጉበት ንቅለ ተከላ ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች ለመስጠት የሚያስችል የህክምና ክፍል ለመመስረት የሙያ ስልጠናዎች እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ቆይተዋል። ኢትዮጵያ ሄፐታይተስ ቢ እና ሄፐታይተስ ሲ በተሰኙት የጉበት በሽታ ተጠቂዎች ከፍተኛ ከሆነባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት ከሶት ወራት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ…
Read More
ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰኛ ጊዜን አራዘመች

ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰኛ ጊዜን አራዘመች

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን እንዲወስን በተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቦ ነበር የገንዘብ ሚኒስቴር ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ 91.4 ቢሊየን ብር በጀት ይፋ ተደርጓል፡፡ መንግስት ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ እንደሚያደርግ ከአንድ ወር በፊት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ የደመወዝ ጭማሪ 2.3 ሚሊየን የፌደራልና የክልል መንግስታት የመንግስት ሰራተኞች፣ 56 ሺህ ተሿሚዎች፣ ለሀገር ደህንነት ሲባል ቁጥራቸው የማይቀመጠው የክልል ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ አካላትን ጨምሮ የደሞዝ ማሻሻያው ተጠቃሚ ናቸው ተብሏል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ለዝርዝር የደሞዝ መግለጫው በፃፉት መግቢያ "በተለይም ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ እና ሊደርስ የሚችለውን የኑሮ ጫና በመጠኑም ቢሆን ለመቋቋም እንዲችሉ" የሚል አገላለፅ ተጠቅመዋል፡፡ በጭማሪው…
Read More
ሶማሊያ የኢትዮጵያ አማጺያንን ልታስታጥቅ እንደምትችል አስጠነቀቀች

ሶማሊያ የኢትዮጵያ አማጺያንን ልታስታጥቅ እንደምትችል አስጠነቀቀች

ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት ካደረገች በኋላ ከሶማሊያ ጋር ያላት ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ሻክሯል፡፡ የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞዓሊም ፊኪ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን ስምምነት ከተገበረች የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ታጣቂዎች ልንደግፍ እንችላለን ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ አክለውም “ስምምነቱ ከተተገበረ ታጣቂዎችን አልያም የኢትዮጵያን መንግስት ለመጣል የሚታገሉ አማጺያን ጋር ለመገናኘት እንሞክራለን” ብለዋል፡፡ “እስካሁን ታጣቂዎቹን ለማግኘት እየሞከርን አይደለም፣ ለችግሩ ሁሉ መፍትሄ ሊኖር እንደሚችል ተስፋ አለን” የሚሉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ስምምነቱን ወደ መተግበር ከገባች ግን አማጺያኑን መርዳት የምችልበት መንገድ ይኖራል ሲሉ መናገራቸውን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ህወሃትን ትረዱ ነበር? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም “ተመካክረንበት ነበር፣ ነገር ግን…
Read More
ዮሀንስ አያሌው(ዶ/ር) የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ዮሀንስ አያሌው(ዶ/ር) የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ባለፈው ሳምንት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጤና እክል ምክንያት ከሃላፊነት የለቀቁት ዮሀንስ አያሌው ብሩ (ዶ/ር)፣ የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ  ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሸመዋል፡፡ የአማራ ባንክ በማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ላይ እንዳጋራው ዩሀንስ አያሌው ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በዋና ስራ አስፈጻሚነት መሾማቸውን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ በሰባት ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ከሁለት ዓመት በፊት ስራ የጀመረው የአማራ ባንክ 138 ሺህ ባለ አክስዮኖች የመሰረቱት የግል ባንክም ነው፡፡ ዮሐንስ አያሌው በልማት ባንክ የስራ ዘመናቸው ባንኩ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት  ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዶክተር ዮሀንስ አያሌው ከዚህ ቀደም…
Read More