Teachingenglish

ኢትዮጵያ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ኢትዮጵያ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች

ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት ለመዋዕለ ህጻናት ወይም ኬጂ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዳይማሩ ከልክላ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኬጂ ተማሪዎች እንዳይማሩ አግዶት የነበረውን እንግሊዘኛ ቋንቋ በድጋሚ እንዲሰጥ መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ቢሮው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ክልከላ የጣለው ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ በሚል እንደነበር በወቅቱ ገልጾ ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ተቋርጦ የነበረው የቅድመ መደበኛ (ኬጂ) የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በዚህ ሳምንት በተጀመረው የ2017 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በሳምንት ለአምስት ጊዜ እንደሚሰጥ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ያዘጋጀው የእንግሊዘኛ ቋንቋ የተማሪዎች መፅሐፍ እና የመምህራን መምሪያ ለመንግሥት ትምህርት ቤቶች ተሰራጭቷል። ሕጻናት ወደ አንደኛ ክፍል ከመሸጋገራቸው አስቀድሞ ባለው ቅድመ መደበኛ ደረጃ ለሚማሩ…
Read More