17
Sep
በኢትዮጵያ የጉበት ንቅለ ተከላ ፕሮግራም በትብብር ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ በጤና ሚኒስቴር እና በካሊፎርኒያ ፓሲፊክ የሕክምና ማዕከል መካከል ተፈርሟል። ይህ ተነሳሽነት በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ቅድስት ኪዳኔ ይማም የሚመራ ሲሆን በሰሜን ካሊፎርኒያ ያሉ ባልደረቦቻቸውን በማስተባበር ወደ ተግባር የተቀየረ ነው። ከዚህ ቀደም ዶ/ር ቅድስት አገልግሎቱን በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል የጉበት ንቅለ ተከላ ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች ለመስጠት የሚያስችል የህክምና ክፍል ለመመስረት የሙያ ስልጠናዎች እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ቆይተዋል። ኢትዮጵያ ሄፐታይተስ ቢ እና ሄፐታይተስ ሲ በተሰኙት የጉበት በሽታ ተጠቂዎች ከፍተኛ ከሆነባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት ከሶት ወራት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ…