30
Sep
አዲሱ የሲሚንቶ ፋብሪካ በቀን አንድ መቶ ሃማሳ ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ የማምረት አቅም አለው ተብሏል፡፡ ፋብሪካው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል፡፡ ፋብሪካው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ልዩ ቦታው ለሚ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የተገነባ ሲሆን ፋብሪካው ከአዲስ አበባ በ134 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው። ተገንብቶ ለመጠናቀቅ ሁለት አመታትን ብቻ የወሰደው ፋብሪካ ዘመናዊ የሆነ ከሰው ንክኪ የራቀ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም በመሆኑ የበለጠ ምርት ለማምረት የቀነሰ ኃይል የሚያስፈልገው ነው ተብሏል። በተለይም 174 ሜትር ርዝመት ያለው በአለም ረዥሙ የሆነውን የቅድመ ማሞቂያ ማማ እንደያዘ በምረቃው ወቅት ተገልጿል። የፋብሪካው የማምረት አቅም ከዚህ በፊት በማምረት ላይ ያሉ ተመሳሳይ ፋብሪካዎች ተደምረው የሚያመርቱትን ሃምሳ…