Roboticcompletion

ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦት ውድደር ላይ አሸነፉ

ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦት ውድደር ላይ አሸነፉ

195 ሀገራት በተሳተፉበት የሮቦቲክስ ውድድር ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ እድሜያቸዉ ከ14 እስከ 18 የሆኑ 5 ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ከመስከረም 14 እስከ 20 በግሪክ በተከሄደው ዓለም አቀፉ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ከ195 በላይ ሀገራት በሚያሳትፈዉ የሮቦቲክስ ዉድድር  ኢትዮጵያን ወክለዉ ችግሮችን እንዴት መፍታት ይችላሉ የሚለው ላይ ትኩረት አድርገው  በውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ተወዳዳሪዎቹ በ2024 የፈርስት ግሎባል የሮቦቲክስ ቻሌንጅ  ተማሪዎች  በሮቦቲክስ  በኩል  በሳይንስ፣  በቴክኖሎጂ ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ  መስኮች  ማበረታት  ዓላማ ባደረገው የወደ ፊቱን መመገብ የሚል መርህ ያለው ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ ይህ ጭብጥ የሚያተኩረው የአለም የምግብ ዋስትናን እና ዘላቂ የግብርና አሰራሮችን መፍታት ላይ  መሆኑንም ተወዳዳሪዎቹ ተናግረዋል። ኢትዮጲያን የወከሉት ተወዳዳሪዎች ካሌብ ኤርሚያስ፣…
Read More