ዜና

ኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ ግብይትን በይፋ ከለከለች

ኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ ግብይትን በይፋ ከለከለች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “የክሪፕቶ አሴትን”  እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ በቀጣይ ሊያወጣ እንደሚችል ገልጿል፡፡ የተቋሙ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንደገለጹት ብሔራዊ ባንክ የክሪፕቶ ከረንሲ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር  ያሉ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን እያየ መሆኑን ተናግረዋል።  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ16 ዓመት በፊት የወጣውን እና በስራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን አጽድቋል፡፡ በምክር ቤቱ ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት አቶ ማሞ አዲሱ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ድንጋጌዎች መካከል ክሪፕቶ ከረንሲ እና የዲጂታል ገንዘብን መጠቀም የተመለከቱት ይገኙበታል፡፡ የጸደቀው አዋጅ “አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ብሔራዊ ባንክ ካልፈቀደ በስተቀር፤ ክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ሌላ ማንኛውንም ዲጂታል…
Read More
ፕሬዚዳንት ማክሮን ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው ተባለ

ፕሬዚዳንት ማክሮን ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው ተባለ

ፕሬዝዳንት ማክሮን በአዲስ አበባ ቆይታቸው በእድሳት ላይ ያለውን ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ይመርቃሉ ተብሏል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካ ቀንድ ይመለሳሉ ተብሏል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የፊታችን ሐሙስ ማለትም ታህሳስ 11 ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ጉብኝት እንደሚያርጉ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ዘግቧል። በዚህ ጉብኝት ፕሬዝዳንት ማክሮን አዲስ የታደሰውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መንግስትን ይመርቃሉ ተብሏል፡፡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት ላለፉት 18 ወራት ሰፊ እድሳት የተደረገለት ሲሆን ከሚቀጥለው ሳምንት በኋላ ለጎብኚዎች ክፍት ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል። ቤተ መንግሥቱ ከ1955 ጀምሮ ዓ.ም የአፄ ኃይለ ሥላሴ ቤተ መንግስት የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን ላለፉት ዓመታት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ይፋዊ መኖሪያ ሆኖ እና የመንግሥት ሥራ የሚካሄድበት ቦታ…
Read More
ኢትዮጵያ በቱርኩ ያፒ መርከዚ የባቡር ግንባታ ኩባንያ ላይ ክስ መሰረተች

ኢትዮጵያ በቱርኩ ያፒ መርከዚ የባቡር ግንባታ ኩባንያ ላይ ክስ መሰረተች

የቱርኩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ በኢትዮጵያ የጀመረውን የባቡር መስመር ግንባታ ሳያጠናቅቅ ከሀገር ወጥቷል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የቱርኩ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ የአዋሽ-ወልድያ-መቀሌ የባቡር ሐዲድ ግንባታን ሳያጠናቅቅ በመውጣቱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡ ያፒ መርከዚ የተሰኘው የቱርክ ስራ ተቋራጭ ኩባንያ በ2007 ዓ.ም 392 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የባቡር መስመር ግንባታ በማካሄድ ላይ ነበር፡፡ ይህ የባቡር መስመር የመካከለኛ እና ሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከጅቡቲ ወደብ ጋር የተሳለጠ የትራንስፖርት እንቅስቀሴ እንዲኖራቸው ታስቦ በመገንባት ላይ ነበር፡፡ ከቱርኩ ኤግዚም ባንክ በተገኘ 1 ነትብ 9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግንባታው እየተካሄደ የነበረው ይህ የባቡር መስመር ሊጠናቀቅ ጥቂት መሰረተ ልማቶች ሲቀሩት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት…
Read More
በደን አጠባበቅ ላይ የተሻለ የፈጠራ ስራ ያቀረቡ ወጣቶች ተሸለሙ

በደን አጠባበቅ ላይ የተሻለ የፈጠራ ስራ ያቀረቡ ወጣቶች ተሸለሙ

ውድድሩ የኢትዮጵያ አየር ንብረት ለውጥ ትብብር፣ኢንፉሌንሰርስ እና ቬንደንስ የተሰኙ ተቋማት በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡ ሶስቱ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚሰሩት ተቋማት ከሁለት ወራት በፊት ወጣቶች በደን አጠባበቅ ዙሪያ በኢሴይ ራይቲንግ፣ ኢንፎ ግራፊ እና ቪዲዮ የታገዘ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ የኢንፉሌንሰርስ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ናሆም ፈቃዱ እንዳሉት በተደረገው ማስታወቂያ መሰረት 80 ወጣቶች በውድድሩ ላይ እንደተሳተፉ ተናግረዋል፡፡ ከሁሉም ተወዳዳሪዎች ውስጥ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ደረጃ የወጡ ወጣት አሸናፊዎች  ከ10 ሺህ እስከ 20 ሺህ ብር ሽልማት ተሸልመዋል፡፡ ወጣት ናሆም እንዳሉት ተቋማቸው ኢንፉሌንሰርስ ሁሉም ሰው ለአካባቢ ጥበቃ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በሚል መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡ ለአካባቢ ጥበቃ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት ለሚፈልጉ ሰዎች ነው የተቋቋመው፣የአየር ንብረት ለውጥ የባሰ ጉዳት የሚያደርሰው…
Read More
ኢትዮጵያ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዳይሰጥ አገደች

ኢትዮጵያ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዳይሰጥ አገደች

በዩንቨርሲቲዎች የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ እገዳ ተጥሎባቸዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው አሳውቋል፡፡ ከጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት ክፍተት የታየበት "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡ በዚህም ማሻሻያው ተጠናቆ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት ዕድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ "አንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ፣ መመሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት እንደቀጠሉ የትምህርት ሚኒስትር…
Read More
ኢትዮጵያ ኤርትራዊያን ስደተኞች እየተዋከቡ ነው መባሉን አስተባበለች

ኢትዮጵያ ኤርትራዊያን ስደተኞች እየተዋከቡ ነው መባሉን አስተባበለች

በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች በመንግሥት እየተዋከቡ ነው መባሉን የስደተኞችና ተመላሾች አግልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል፡፡አገልግሎቱ በመግለጫው በኢትዮጵያ የተጠለሉ ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡ ከሰሞኑ እንደ በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጨምሮ በስፋት የተዘገበው የኤርትራዊያን በአዲስ አበባ መዋከብ ከእውነታው የራቀ ነው በማት አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ በሚገኙ በኤርትራውያን ላይ የጅምላ እስራት እየተፈጸመባቸው መሆኑ ከሰሞኑ ሲዘገብ ነበር፡፡ ምንም እንኳን መሰል ክስተቶች አዲስ ባይሆኑም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የጅምላ እስራት ግን ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ኤርትራውያን ከሰሞኑ ለቪኦኤ መናገራቸው ይታወሳል።ይሁን እንጂ የስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው አገልግቱ በሰጠው ምላሽ በኢትዮጵያ የሚገኙ…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ስምምነቱን ተከትሎ ሶማሊያ ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው በሚል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣም ነበር፡፡ የሁለቱም ሀገራት ወዳጅ የሆነችው ቱርክ በአንካራ የውይይት መድረክ ያዘጋጀች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በትናንትናው ዕለት ወደ አንካራ አቅንተው ነበር፡፡ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የሁለቱን ሀገራት መሪዎች በተናጠል አግኝተው እንዳወያዩ አናዶሉ ዘግቧል፡፡ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ኢትዮጵያ እና ሱማልያ ሀለቱንም ሀገራት በሚያግባባ መልኩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ኤርዶጋን ሁለቱ ሀገራት በጋራ ይፋ የሚያደርጉት የስምምነት ዶክመንት እንደተዘጋጀ ጠቅሰው ዶክመንቱ ሀገራቱ የበፊቱን ሳይሆን መጪውን ግዜ እንዴት በጋራ አብረው ተከባብረው እና በመልካም ጉርብትና እንደሚወጡት…
Read More
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎች ስራ መጀመራቸውን ገልጿል። የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ  "የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎችን ስራ አስጀምሯል " ሲል ይፋ አድርገዋል። "ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ አክለዋል። ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነውም ተብሏል። በርበራ ወደብ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World ይተዳደራል የተባለ ሲሆን የበርበራ ወብ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው…
Read More
በኢትዮጵያ የአንበሳ እንስሳት የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

በኢትዮጵያ የአንበሳ እንስሳት የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን  የአንበሳ እና የስጋ በል እንስሳት ተመራማሪ የሆኑት አቶ ካህሳይ ገብረ-ተንሳይ  አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያሉት አንበሶች ቁጥር ከ1 ሺ እንደማይበልጥ ተናግረዋል። በሃገሪቱ አሁን ላይ አንበሶች ያሉበት  ሁኔታ ለማወቅ ጥናት  ማድረጋቸውን የገለፁልን ተመራማሪው በአዋሽ  እና በመካከለኛው አዋሽ  በተደረገው ጥናት መሰረት ያለው ሁኔታ  ተስፋ ሰጪ ቢሆንም   አሁንም ግን ሁሉም ርብርብ ካላደረገ  አንበሶቹን ልናጣ እንችላለን ብለዋል፡፡ ተመራማሪው እንደሚሉትም ህገወጥ የነዋሪዎች ሰፈራ፣ የደን ጭፍጨፋ መኖር፣ የእርሻ ስራ እና  ግጦሽ  መበራከት አንበሶቹ  የሚፈልጉትን ምግብ እንዳያገኙና በምግብ ሰንሰለት ውስጥ ችግር እንዲፈጠር ብሎም ለህገወጥ አደን  በስፋት ተጋላጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ  የባህል መድኃኒት ቀማሚዎች  ፊታቸውን ወደ አንበሳ አጥንት ማዞራቸው እንስሳቶቹን ለህገወጥ…
Read More
ዳሸን ባንክ ዘ ባንከር የተሰኘውን ሽልማት አሸነፈ

ዳሸን ባንክ ዘ ባንከር የተሰኘውን ሽልማት አሸነፈ

ዳሸን ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ባስመዘገበው የላቀ አፈጻፀም የ“ዘባንከር” ሽልማት ተሸላሚ ሆነ ባንኮችን በተለያዮ የምርጥ አፈጻጸም መለኪያዎች የሚመዝነው የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚያሳትመው ዘባንከር መጽሔት ዳሸን ባንክ የ2024 የኢትዮጵያ አሸናፊ ሆኗል፡፡  የዳሸን ባንክ ቺፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን ወ/ሪት እየሩሳሌም ዋጋው እና የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፋይናንስ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በእንግሊዝ ሎንዶን ተገኝተው ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡  በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለፀው ዳሸን ባንክ በዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ከተለያዩ አለምአቀፍና አህጉራዊ ባለድርሻ አካላት ጋር የፈጠረው ውጤታማ ጥምረት ለሽልማት አብቅቶታል ተብሏል፡፡  አቶ ሙሉጌታ አለባቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሽልማቱ ዳሸን ባንክ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አማካኝነትና እና ከተለያዩ አለም አቀፍና አህጉራዊ ተቋማት…
Read More