ዜና

ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ከወራት በፊት በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት የተዘጋጀው “የጤና አገልግሎት አስተዳደር አዋጅ” በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡ ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ያልተለመዱ እና አዳዲስ የጤና አገልግሎቶች ለዜጎች እንዲሰጡ ይፈቅዳል፡፡ ለአብነትም በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ባለትዳሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚለው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አተነፋፈሳቸው በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሰዎች ህይወታቸው ስለሚቋረጥበት ሁኔታም በአዋጁ ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረትም በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን እንዲቋረጥ የሚፈቅድ ሲሆን ይህም የሚቻለው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው። የዚህ ስርዓት አተገባበር መመሪያን በቀጣይ የጤና ሚኒስቴር እንደሚያወጣ የተገለጸ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ታሪክ…
Read More
በኢትዮጵያ ባንድ ቀን ውስጥ ከ14 ጊዜ በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ

በኢትዮጵያ ባንድ ቀን ውስጥ ከ14 ጊዜ በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች እየተደጋገሙ ሲሆን እስካሁን መኖሪያ ቤቶች ላይ የተወሰኑ ጉዳቶችን ከማድረስ የዘለለ ከባድ ጉዳት አላደረሱም፡፡ አደጋው እያጋጠመ ያለው በአፋር ክልል አዋሽ ልዩ ስሙ ፈንታሌ አካባቢ እንደሆነ የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ በአዋሽ ፈንታሌ እየተከሰተ ባለዉ ተደጋጋሚ ርዕደ መሬት ምክንያት ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እየለቀቁ ሲሆን እስካሁን ከ2,500 በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ በተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች እስካሁን ከፍተኛው 5 በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው። በአደጋው ከ100 በላይ ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ሲሆን፤ 2 ሺሕ 560 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና እንሰሳት መሞታቸውን የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳደር አቶ አደም ባሂ ተናግረዋል። አስተዳዳሪው አክለውም በቀን ውስጥ እስከ…
Read More
ሙሽራዋ በሰርጓ ዕለት የባሏን ሞት ተረዳች

ሙሽራዋ በሰርጓ ዕለት የባሏን ሞት ተረዳች

በሀዋሳ አቅራቢያ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ ሙሽራውን ጨምሮ 74 ሰዎች ሞተዋል። በትናንትናው ዕለት በሲዳማ ክልል፣ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ልዩ ስሙ ጋላና ድልድይ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ተገልብጦ ሙሽራውን ጨምሮ የ74 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ ማቴ መንገሻ (ዶ/ር) እንዳሉት "አይሱዚው 11 ሰዓት አካባቢ መነሻዉን ቦና ወረዳ ሚሪዴ ገጠር ቀበሌ አድርጎ ወራንቻ ወደተባለ አጎራበች ቀበሌ የወንድ ወገን የሆኑ ከ70 በላይ ሰርገኞችን ጭኖ ወደ ሴቷ ቤት ጉዞ ላይ ነበር " ብለዋል። ገላና ድልድይ ላይ ሲደርስ ግን ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ እስካሁን በተጣራዉ በአጠቃላይ የ74 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አረጋግጠዋል። በ4 ሰዎች ላይ ከፍተኛ…
Read More
የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞቹ ታገቱ

የትግራይ ቲቪ ጋዜጠኞቹ ታገቱ

ሚዲያው እንደገለጸው ከህገወጥ የወርቅ ማውጣት ሂደት ጋር በተያያዘ መረጃ በማሰባሰብ ላይ የነበሩ ጋዜጤኞቹ  በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል። በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ያለውን ህገወጥ የወርቅ ማዕድን የማውጣት ሂደትና የጎንዮሽ ጉዳቶቹ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ዘገባ ለመስራት ወደ ስፍራው ያቀናው የጋዜጠኞች ቡድን በታጣቂዎች ታግተዋል ሲል ተገልጿል። ሶስት ባለሙያዎችን የያዘው የጋዜጠኞች ቡድኑ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ/ም ጥዋት 3 ሰዓት በአስገደ ወረዳ፣ መይሊ ከተባለው ስፍራ ወጣ ብሎ በሚገኘውን መንደር በታጣቂዎች ተይዘዋል ተብሏል። ጋዜጠኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት በቦታው ተገኝተው ስላለው ነገር ከአካባቢው ነዋሪዎች መረጃዎችን ሲያሰባስቡ የቆዩ ሲሆን በተለይም በመይሊ አካባቢ ማዕድናቱን ለማውጣት በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙ የተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች እያደረሱት ያለውን ጉዳት በተመለከተ መረጃዎች…
Read More
ኢትዮጵያ በአዲሱ የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስስ ሳትካተት ቀረች

ኢትዮጵያ በአዲሱ የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስስ ሳትካተት ቀረች

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ልዑክ (አትሚስ) የስራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (አውሶም) እንዲተካው ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ምክር ቤቱ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ አልሸባብን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪዎች ከቀናት በኋላ አዲሱን ተልዕኮ እንዲጀምሩ ፈቅዷል፡፡ ውሳኔውን ለማጸደቅ ትላንት በተደረገው ድምጽ አሰጣጥ ላይ ከ15 አባል ሀገራት በ14ቱ ድጋፍ ያገኝ ሲሆን ለሰላም አስከባሪ ሀይሉ በሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ቅሬታ ያነሳቸው አሜሪካ በድምጸ ተአቅቦ ወጥታለች፡፡ ቀደም ሲል በጸደቀው የምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በሶማሊያ የሚሰማሩ የሰላም አስከባሪ ሀይሎችን 75 በመቶ ወጪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚሸፍን ይገልጻል፡፡  በምክር ቤቱ ድምጽ መስጠት የማይችሉት ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ…
Read More
በኢትዮጵያ የስራ ማቆም አድማ ሊደረግ እንደሚችል ተገለጸ

በኢትዮጵያ የስራ ማቆም አድማ ሊደረግ እንደሚችል ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አባል ማህበራት የሰራተኞች ጥያቄ ካልተመለሱ  ስራ የማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በመንግስት እንዲወሰንና ከደመወዝ ላይ የሚቆረጠው ከፍተኛ_ግብር እንዲቀንስ መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ አልሰጠም ተብሏል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ሰራተኞች ወደ ስራ ማቆም አድማና ወደ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያመሩ እንደሚችሉ ማህበራቱ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የኢትዮጵያን ሰራተኞች ይወክላሉ ከሚባሉት አባላቱ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት አድርጎት በነበረው ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ አባላቱ በሰራተኞች ጥቅም ዙሪያ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ማህበራቱ በመግለጫቸው እስካሁን ስናነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎቻችን በመንግስት ባለመመለሳቸው ከዚህ በኋላ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንዲሁም በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንገደዳለን ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የውጭና ህዝብ…
Read More
ኢትዮጵያ በሶማሊያ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ በሶማሊያ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ስምምነቱን ተከትሎ ሶማሊያ ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው በሚል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣም ነበር፡፡ የሁለቱም ሀገራት ወዳጅ የሆነችው ቱርክ በአንካራ የውይይት መድረክ ያዘጋጀች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በአንካራ መስማማታቸውን ከሁለት ሳምንት በፊት ተናግረው ነበር፡፡ በቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አደራዳሪነት የተስማሙት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አንዳቸው የሌላኛቸውን ሉዓላዊነት ለማክበር ኢትዮጵያም የወደብ አገልግሎት ከሶማሊያ እንደምታገኝ ተስማምተውም ነበር፡፡ ከአንካራው ስምምነት በኋላ የሶማሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የደህንነት ባለስልጣናት ወደ አዲስ አበባ መጥተው ተወያይተዋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ሬድዋን ሁሴን የሶማሊያ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት…
Read More
በሐረር ከተማ 35 የባንክ ቅርንጫፎች ለኮሪደር ልማት ገንዘብ አላዋጣችሁም በሚል ታሸጉ

በሐረር ከተማ 35 የባንክ ቅርንጫፎች ለኮሪደር ልማት ገንዘብ አላዋጣችሁም በሚል ታሸጉ

የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር በሐረር ከተማ የታሸጉ 35 የባንክ ቅርንጫፎች ተከፍተው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ እንዲደረግ ለሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቤቱታ አቅርቧል። የክልሉ መንግስት ቅርንጫፎቹ የታሸጉት “ግንባታቸው ባላለቁ ህንጻዎች አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ ነው” ቢልም፤ ማህበሩ ግን ከሌሎች የንግድ ድርጅቶች በተለየ መልኩ እርምጃው በእነርሱ ላይ መወሰዱ ለክልሉ የኮሪደር ልማት የተጠየቀው መዋጮ ተግባራዊ ባለመደረጉ ምክንያት የተፈጸመ እንደሆነ “ከድምዳሜ ላይ እንዲደርስ” እንዳደረገው ገልጿል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። በሀረሪ ክልል የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ባንኮች የሁለት ሚሊዮን ብር “ድጋፍ” እንዲያደርጉ በደብዳቤ የተጠየቁት የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ ነበር። ደብዳቤውን ለባንክ ቅርንጫፎች የጻፈው የሀረሪ ክልል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ፤ የገንዘብ መጠኑን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ…
Read More
አቶ ካሳሁን ፎሎ በድጋሚ የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

አቶ ካሳሁን ፎሎ በድጋሚ የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ (ኢሠማኮ) በአዲስ አበባ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ኮንፌዴሬሽኑን በቀጣዮቹ 5 ዓመታት አመራሮችን መርጧል፡፡ በዚህም ላለፉት ዓመታት ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሶስተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋ፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ አቶ ድሪብሳ ለገሰ እና አቶ አብዱልሐኪም ሙሰማ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ እንደመረጠም ሰምተናል፡፡ አቶ ካሳሁን ከምርጫው በኋላ ባደረጉት ንግግር በሀላፊነት የሚቀጥሉት ለመጨረሻ ጊዜ እንደሆነ በጉባኤው ላይ ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም መንግሥት ለሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን በድጋሚ ጠይቀዋል። ካሳሁን፣ መንግሥት ሠራተኞች በሚከፍሉት የደመወዝ ገቢ ግብር ላይ ቅናሽ እንዲያደርግ ኢሠማኮ በተደጋጋሚ ሲጠይቀው ለነበረው ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥም አሳስበዋል። በዓለማቀፍና የአገር ውስጥ ችግሮች ሳቢያ ሠራተኞች የኑሮ ውድነቱን ሊቋቋሙት ከሚችሉት በላይ…
Read More
ቴክኖ ሞባይል  በኤይ አይ የታገዙ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋወቀ

ቴክኖ ሞባይል  በኤይ አይ የታገዙ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋወቀ

ቴክኖ ሞባይል የቴክኖ ኤአይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን አስተዋውቋል፡፡ ቴክኖ ሞባይል በቅርቡ ለዓለም ያስተዋወቀው የቴክኖ ኤአይ አጋዥ መተግበሪያን እና አዳዲስ በኤይ አይ የታገዙ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል፡፡ አዲሱ የቴክኖ ኤአይ (Tecno AI) አጋዥ ቴክ ቋንቋን ከመተርጎም አንስቶ ፎቶን በራሱ አቅም ኤዲት ማድረግ፣ የተለያዩ ድምጾችን ወደ ፅሁፍ መቀየር እና መሰል ተያያዥ ስራዎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመስራት የሚያስችል አጋዥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ተካቶለታል ተብሏል፡፡ የቴክኖ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሊክ "ቴክኖ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ጉልህ ሚናን እየተጫወተ እንደሚገኝ" ጠቅሰዋል። አቶ አሊክ "ቴክኖ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆኑን…
Read More