assisteddying

ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ከወራት በፊት በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት የተዘጋጀው “የጤና አገልግሎት አስተዳደር አዋጅ” በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡ ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ያልተለመዱ እና አዳዲስ የጤና አገልግሎቶች ለዜጎች እንዲሰጡ ይፈቅዳል፡፡ ለአብነትም በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ባለትዳሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚለው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አተነፋፈሳቸው በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሰዎች ህይወታቸው ስለሚቋረጥበት ሁኔታም በአዋጁ ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረትም በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን እንዲቋረጥ የሚፈቅድ ሲሆን ይህም የሚቻለው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው። የዚህ ስርዓት አተገባበር መመሪያን በቀጣይ የጤና ሚኒስቴር እንደሚያወጣ የተገለጸ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ታሪክ…
Read More
መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ

መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ

መዳን የማይችሉ ሰዎችን ህይወት ማቋረጥ የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት ባሳለፍነው ሳምንት የቀረበው ይህ ረቂቅ አዋጅ "የጤና አገልግሎት አስተዳደር አዋጅ" ተብሎ ቀርቧል፡፡ በዚህ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ በርካታ ከጤና ጋር የተያያዙ ስርዓቶች የቀረቡ ሲሆን በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ባለትዳሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ የህክምና አገልግሎት ስለሚያገኙበት መንገድ ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አተነፋፈሳቸው በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሥርዓት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ የሚደነግግ ረቂቅ ህግም ለምክር ቤቱ ቀርቦለታል፡፡ የዚህ ረቂቅ ህግ አላማም የሃገሪቱን እድገት ለማሳለጥና የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል በሚደረግ ጥረት የልማቱ አንቀሳቃሽ የሆነውን ሕዝብ ጤንነት በተሟላ ሁኔታ መጠበቅ እንደሆነ ተጠቅሷል። በዚህ ረቂቅ ህግ መሰረት በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን…
Read More