organdonation

ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ኢትዮጵያ በሕክምና ባለሙያዎች የታገዘ ሞት እንዲፈጸም ፈቀደች

ከወራት በፊት በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት የተዘጋጀው “የጤና አገልግሎት አስተዳደር አዋጅ” በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡ ይህ አዋጅ በኢትዮጵያ ያልተለመዱ እና አዳዲስ የጤና አገልግሎቶች ለዜጎች እንዲሰጡ ይፈቅዳል፡፡ ለአብነትም በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ባለትዳሮች በቴክኖሎጂ የታገዘ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚለው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አተነፋፈሳቸው በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ ሰዎች ህይወታቸው ስለሚቋረጥበት ሁኔታም በአዋጁ ላይ ተደንግጓል፡፡ በዚህ አዋጅ መሰረትም በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን እንዲቋረጥ የሚፈቅድ ሲሆን ይህም የሚቻለው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው። የዚህ ስርዓት አተገባበር መመሪያን በቀጣይ የጤና ሚኒስቴር እንደሚያወጣ የተገለጸ ሲሆን ረቂቅ ህጉ በኢትዮጵያ ታሪክ…
Read More