01
Mar
በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው ከሰም የስኳር ፋብሪካ፣ በክልሉ እየተከሰተ ባለው ለወራት የቀጠለ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይፋ ባደረገ በወሩ፣ ከ3,700 በላይ ሠራተኞቹን ከሥራ ማሰናበቱ ታወቀ። በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በካምፕ የተጠለሉ 3,750 ቋሚና ጊዜያዊ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፣ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባልጠበቁት ሁኔታ ከሥራ ተሰናብተዋል። ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 123 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ከሰም ስኳር ፋብሪካ ከ10 ዓመት በፊት ነበር ስኳር ማምረት የጀመረው፡፡ በዓመት 260 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም የነበረው ይህ ስኳር ፋብሪካ በአዋሽ አካባቢ ባጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ስራ አቁሟል፡፡ በ20 ሺህ ሄክታር መሬት…