04
Sep
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቴላቪቭ በሃይለኛ ግጭት ውስጥ የተሳተፉ ኤርትራውያን በአስቸኳይ እንዲባረሩ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። የሀገሪቱን አፍሪካውያን ስደተኞች በሙሉ ለማስወገድ እቅድ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። ይህንን አስተያየት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት በደቡባዊ ቴል አቪቭ በኤርትራ ተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል በነበረ ደም አፋሳሽ ግጭት በርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት ከደረሰ ከአንድ ቀን በኋላ ነበር። ኔታንያሁ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ በትላንትናው እለት በተጠራው ልዩ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ “በሁከት ፈጣሪዎች ላይ ከባድ እርምጃዎችን እንፈልጋለን ፣ የተሳተፉትን ወዲያውኑ ወደ መጡበት መመለስ እንፈልጋለን” ብለዋል ። ሚኒስትሮቹ “ሌሎች ህገወጥ ሰርጎ ገቦችን ለማስወገድ” እቅድ እንዲያቀርቡላቸው የጠየቁ ሲሆን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ስደተኞቹን ለቀው እንዲወጡ ለማስገደድ የታቀዱ አንዳንድ እርምጃዎችን መተላለፉን በንግግራቸው አስታውቀዋል። በአለም አቀፍ ህግ…