16
Dec
የቱርኩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ በኢትዮጵያ የጀመረውን የባቡር መስመር ግንባታ ሳያጠናቅቅ ከሀገር ወጥቷል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የቱርኩ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ የአዋሽ-ወልድያ-መቀሌ የባቡር ሐዲድ ግንባታን ሳያጠናቅቅ በመውጣቱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡ ያፒ መርከዚ የተሰኘው የቱርክ ስራ ተቋራጭ ኩባንያ በ2007 ዓ.ም 392 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የባቡር መስመር ግንባታ በማካሄድ ላይ ነበር፡፡ ይህ የባቡር መስመር የመካከለኛ እና ሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከጅቡቲ ወደብ ጋር የተሳለጠ የትራንስፖርት እንቅስቀሴ እንዲኖራቸው ታስቦ በመገንባት ላይ ነበር፡፡ ከቱርኩ ኤግዚም ባንክ በተገኘ 1 ነትብ 9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግንባታው እየተካሄደ የነበረው ይህ የባቡር መስመር ሊጠናቀቅ ጥቂት መሰረተ ልማቶች ሲቀሩት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት…