ኢኮኖሚ

አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት ከአለም አቀፉ አሚአ ፓወር ኩባንያ ጋር ተስማምታለች፡፡ ስምምነቱ በዱባይ ከአራት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ እና አሚአ ኩባንያ ሀላፊዎች መካከል ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ለሚገነባዉ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ለማልማት በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ከተሰማራው እና መቀመጫዉን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ካደረገዉ ከአሚአ ፓወር ጋር ስምምነት አድርጓል። በታዳሽ ኃይል ልማት፣ ግንባታና አስተዳደር ዘርፍ የተሰማራው አሚአ ፓወር በአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል 300 ሜጋ ዋት አመንጭቶ ለኢትዮጵያ ለመሸጭ ነው ሥምምነቱን የፈረመው። በኢትዮጵያ 300 ሜጋ ዋት የንፋስ ሃይል ፕሮጀክትን ለማልማት እና ለማንቀሳቀስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር የኃይል ግዢ ስምምነት እና የትግበራ ስምምነት መፈራረሙን ያስታወቀው…
Read More
ኢትዮጵያ በሐምሌ ወር በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ወደ ውጭ መላኳ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በሐምሌ ወር በታሪክ ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና ወደ ውጭ መላኳ ተገለጸ

ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ድረስ በአንድ ወር ውስጥ ለሽያጭ ካቀረበችው ቡና በአዲሱ የ2017 በጀት አመት ሀምሌ ወር ከፍተኛ ገቢ ማግኘቷ ተሰምቷል፡፡ በ2017 በጀት አመት ሀምሌ ወር ከቡና ሽያጭ ከ180 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል። የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳህለማርያም ገብረ መድህን እንደተናገሩት  ይህ አፈጻጸም እስከዛሬ ድረስ  በሁሉም የሀምሌ ወራት  ከተገኘው ገቢ  ጋር ሲነጻጸር ሪከርድን የሰበረ ነው ብለዋል። በበጀት ዓመቱ ሀምሌ ወር ለውጪ ገበያ ከቀረበዉ 40 ሺህ 532 ቶን ቡና ከ180 ሚሊዮን  ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል፡፡ በዚህም  እስከዛሬ ድረስ በአንድ ወር ውስጥ ለውጭ ገበያ  ቀርቦ ከተገኘው  ገቢ አኳያ ሲነጻጸር ሪከርድን  መስበር ችሏል፡፡ከእቅድ አንፃር …
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 100 ሚሊዮን መንገደኖችን የሚያስተናገድ ኤርፖርት ሊያስገነባ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 100 ሚሊዮን መንገደኖችን የሚያስተናገድ ኤርፖርት ሊያስገነባ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ጣቢያ ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል። በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው አውሮፕላን ጣቢያ በቢሾፍቱ ከተማ እንደሚገነባ ገልጿል። ይህ አውሮፕላን ጣቢያ ወይም ኤርፖርት የሚገነባው በዓመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን ብቻ የማስተናገድ ያለው ቦሌ ዓከም አቀፍ ኤርፖርትን ለመተካት እንደሆነ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል። በቢሾፍቱ ልዩ ስሙ አቡ ሴራ በተባለው ስፍራ የሚገነባው ይህ ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን ዳር የተሰኘው ኩባንያ መመረጡንም አቶ መስፍን ገልጸዋል። አቶ መስፍን አክለውም አዲሱ ኤርፖርት ግንባታ በአምስት ዓመታት ውስጥ በሁለት ዙር ይገነባል ያሉ ሲሆን ለመጀመሪያው ዙር ግንባታ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደርግበታልም ብለዋል። ኤርፖርቱ ባንድ ጊዜ አራት አውሮፕላኖችን የማሳረፍ እና መንደርደሪያ…
Read More
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሸለሙ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሸለሙ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክተዋል። የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክታለች። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለአሜሪካዊያን አገልግሎት የሰጡ ተቋማትን እና ግለሰቦችን የህይወት ዘመን ሽልማት ይሰጣል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 25 ዓመታት በአሜሪካ ለሚኖሩ ዜጎች በሰጠው አገልግሎት የህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆኗል። አየር መንገዱ ሽልማቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ "ሽልማቱ ለሰጠው አገልግሎት እውቅና የሰጠ ነው" ብሏል። ፕሬዝዳንት ባይደን የፈረሙበት ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች በአትላንታ በተዘጋጀ መርሀግብር ላይ ተቀብለዋል ተብላል። የአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ሽልማቱ ባለፉት ዓመታት ለሰጠው የአቪዬሽን አገልግሎት እውቅና ባለፈ ዓለም አቀፍ ትብብሮችን እንዲያሰፋ…
Read More
ብሔራዊ ባንክ በልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ ዶላርን በ107 ነጥብ 9 ብር ሸጠ

ብሔራዊ ባንክ በልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ ዶላርን በ107 ነጥብ 9 ብር ሸጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ባንክ ለባንኮች ዶላር ለመሸጥ ያወጣው ልዩ ጨረታ ውጤትን ይፋ አድርጓል። በዛሬው እለት በተካሄደው ልዩ ጨረታ 27 ባንኮች የሚፈልጉትን የዶላር መጠን እና የሚገዙበትን ዋጋ አስገብተው ተጫርተዋል። ባንኮቹ ለአንድ የአሜሪካ ዶላር ያቀረቡት አማካይ የመግዣ ዋጋ 107.9 ብር መሆኑን ባንኩ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ጨረታው በነገው እለት ባንኮች በሚያወጡት እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ እንዲመጣ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ብሏል ብሔራዊ  ባንክ። የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ የዶላር ሽያጭ ጨረታው ውጤትን ሲገልጹ ባለፉት ቀናት በባንኮች እና በብላክ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት እየጠበበ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የውጭ ምንዛሬ መረጋጋትን ያመጣል ያሉት አቶ ማሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሁሉንም የውጭ ምንዛሬ እንቅስቃሴ ወደ ባንክ ስርአት የማስገባት እቅድ…
Read More
የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ብር ደረሰ

መንግስት 550 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አዘጋጅቷል ከሁለት ወር በፊት 970 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጽድቆ የነበረው የፌደራል መንግስት ግማሽ ትሪሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዳሉት የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ  ተናግረዋል። መንገስት ካቀረበው 550 ቢሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ "ለማኅበራዊ ድጋፍ " የሚውል ነው የተባለ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለሰራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣ ለመድሃኒት ድጎማ፣ ለለነዳጅ ድጎማ እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ድጎማ እንደሚውል ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ የፌደራል መንግስት የበጀት ማስተካከያ ያደረገው ከዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ በብድር እና እርዳታ ማግኘቱን ተከትሎ ነው፡፡…
Read More
ጸረ ሙስና ኮሚሽን የ113 አመራሮችን ሃብት እያጣራ መሆኑን አስታወቀ

ጸረ ሙስና ኮሚሽን የ113 አመራሮችን ሃብት እያጣራ መሆኑን አስታወቀ

የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2016 በጀት አመት ሃብታቸውን ካስመዘገቡት አመራሮች መካከል በተጨማሪም የሃብት ማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በአንድ መቶ አስራ ሦስት ውሳኔ ሰጪ አመራሮች ላይ የሃብት ማጣራት ስራ እየሰራ መሆኑን የኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በላይነህ ተናረዋል፡፡ ያስመዘገቡት ሃብት አጠራጣሪ ሁኖ በተገኙና በተደረጉ ጥቆማዎች መሰረት በውሳኔ ሰጪ አመራሮች ላይ የሃብት ማጣራት ሥራ እየተሰራ እንዳለ ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡ ኮሚሽኑ በሚሰራው የሃብት ማጣራት ሥራ ሃታቸው ለሙስና የተጋለጡትን ለፍትህ ሚኒስቴር እንደሚሳውቅም ጠቁመዋል፡፡ ሃብታቸው እየተጣራ ያሉትን ውሳኔ ሰጪ አመራሮች በአሁኑ ሰዓት ይፋ ማድርጉ ያልተመዘገቡ ሃብቶችን እንዲያሸሹ ስለሚያደርግ ከማጣራት ሥራው በኋላ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ ከህብረተሰቡ ጋር በይበልጥ…
Read More
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

የዓለም ባንክ የዳይሬክቶች ቦርድ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኢትዮጵያ የ16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ የዓለም ባንክ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫው የገንዘብ ድጋፍና ብድሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን አስታውቋል። በዚህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው ባንኩ፤ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የተራዘመ ብድር ነው ብሏል። የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት 1 ቢሊዮን ዶላር የቀጥታ እርዳታ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ማራዘሚያ እንዲሁም 320 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር በሚል…
Read More
ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧን በ31 በመቶ አዳከመች

ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧን በ31 በመቶ አዳከመች

ኢትዮጵያ ከዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች፡፡ ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በዲሱን የምንዛሬ ተመን ዛሬ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ማሻሻውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫው የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት መሸጋገሩን አስታውቋል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ74.7364 ብር እየተገዛ በ76.2311 እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል። ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ የ18 ብር ጭማሪ ታይቷል። በኢትዮጵያ ንግድ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ቢሊዮን ዶላር አተረፈ

የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ 7 ቢሊዮን ዶላር ማትረፉን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሰጠው መግለጫ በተያዘው በጀት ዓመት 7.02 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል። የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ ይህ ትርፍ ከባለፈው ከመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ጭማሪ አለው ብለዋል። ትርፉ በኢትዮጵያ ብር ሲሰላ 402 ቢሊዮን ብር እንደሚሆን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል። ስራ አስፈጻሚው እንደገለጹት አየርመንገዱ 577,746 የበረራ ሰአቶችን ማስመዝገቡን እና ይህም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ19 በመቶ ጭማሪ አለው።  በበጀት አመቱ 17.1 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የገለጸው አየር መንገዱ ከእነዚህ ውስጥ 13.4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለምአቀፍ መንገደኞች ሲሆኑ 3.7 ሚሊዮን የሚሆኑን ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ናቸው ብሏል።…
Read More