01
Mar
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የውሃ አቅርቦት ችግር እንዲፈታ እና የውሃ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የተኮሱ የፀጥታ ኃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ በመጠየቅ ከቤት ያለመውጣት አድማ መምታታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ከቤት ያለመውጣት አድማው ከተጀመረ ቀናት መቆጠራቸውን የተናገሩት ነዋሪዎች የከተማዋ እንቅስቃሴም ሙሉ በሙሉ ተገድቧል ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በከተማዋ ለወራት የተቋረጠው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንዲፈታ ለመጠየቅ ባለፈው ሳምንት ጄሪካን ይዘው አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የፀጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን እና ቢያንስ 30 ሰዎች የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች እና ኢሰመኮ ማስታወቃቸው ይታወሳል። በከተማዋ ትራንስፖርት፣ የባንክ አገልግሎት፣ የመገበያያ መደብሮችም ሆነ የትኞቹም የመንግሥት ተቋማት ተዘግተው ከተማዋ ጭር ብላ መሰንበቷን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ሰኞ ምሽት…