ኢኮኖሚ

መንግስት አራት ድርጅቶችን ወደግል ሊያዛውር መሆኑን ገለጸ

መንግስት አራት ድርጅቶችን ወደግል ሊያዛውር መሆኑን ገለጸ

መንግስት አራት ድርጅቶችን ወደግል ለማዛወር ማቀዱ ተገለጸ መንግስት የተወሰኑ ተቋማትን ወደግል የማዛወር እቅድ እንዳለው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ኃይለሚካኤል በሰጡት ማብራሪያ፤ በመንግስት የአክሲዮን ድርሻ ተይዘው ያሉ ተቋማት አሉ፡፡ እነርሱን ባለሃብቶች እንዲገቡበት ይፈለጋል ብለዋል፡፡ በመንግስትና በግል አጋርነት ያሉ እንደ ቢ.ኤም ጨርቃጨርቅ፣ አፍሪካ ጁስ፣ አብያታ ሶዳ አሽ እና አምቼ በሂደት ወደግል ባለሀብቶች ለማዛወር መታቀዱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። መንግስት ባለፉት ዓመትት 300 በላይ ድርጅቶችን ወደግል ማዛወሩን ጠቁመው፤በአሁኑ ወቅትም የመንግስትን እና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ መልኩ የነበረው አሰራር የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ ብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ…
Read More
ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ኢትዮጵያዊያን ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች

ቻይና ከ100 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል ሰጠች። የትምህርት እድሉ ከ5 አመታት በፊት የተጀመረው የ "ቻይና ኢትዮጵያ ፍሬንድሽፕ ስኮላርሺፕ አካል" ነው።በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ ለነበሩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው የትምህርት ዕድሉ የተሰጠው። በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ6 ተማሪዎች የሶስተኛ ዲግሪ፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይና ቋንቋ፣ ለ12 ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተማሪዎች የፕሮጀክት ስኮላርሺፕ እና ለአንድ ተማሪ የጥናት ፈንድ የትምህርት እድል ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ የተሰጠው የትምህርት እድል 2 ነጥብ 19 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሆኑም ተገልጿል። የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ጥናትና ምርምር ዘርፍ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሔደው ስነስርዓት…
Read More
ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ

ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ

ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ጠየቁ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና 50 ትሪሊዮን ዶላር ካሳ ልትከፍል ይገባል ብለዋል። የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውሀን ቤተ ሙከራ ውስጥ ማምለጡን የሚናገሩት ትራምፕ ቫይረሱ በአሜሪካ ላይ ላደረሰው ጉዳት ቻይና ካሳ እንድትከፍል ጠይቀዋል ሲል ዴይሊ ሜይል ዘግቧል። አሜሪካ በተደጋጋሚ የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ቤተ ሙከራ አምልጧል በሚል ስትናገር የሚሰማ ሲሆን ቻይና ግን ይህን ክስ ውድቅ አድርጋለች። የኮረና ቫይረስ በዓለም ላይ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ሲገድል አሜሪካ፣ ብራዚል እና ሕንድ ብዙ ዜጎቻቸውን በሞት ያጡ ሀገራት ናቸው።
Read More
ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በሟቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በሟቋረጧ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ብቻ 146 ሚሊየን ዶላር ማጣቷ ተነገረ ቶፕ 10 ቪፒኤን የቴክኖሎጂ ኩባንያ እንዳስታወቀው፣ በትግራይ ክልል የነበረውን ጦርነት ተከትሎ ለአንድ አመት ሙሉ የኢንተርኔት አገልግሎት በመዘጋቱ ሃገሪቱ 146 ሚሊዮን ዶላር ማጣቷን አስታውቋል። አሁንም ቢሆንም በመላው ሀገሪቱ ኢንተርኔት በመቋረጡ ሚሊዮን ዶላሮችን እያጣች ትገኛለች ብሏል። ኢንተርኔት ከተዘጋ ዛሬ 28ኛ ቀኑን የያዙ ሲሆን መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ ያለው ነገር የለም። መንግሥት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት የተሉያዩ አካላት ግፊት በማድረግ ላይ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት እና ኢሰመኮ ከሰሞኑ ኢንተርኔት እንዲለቀቅ ከጠየቁ ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት እቀባ ከሚፈጽሙ ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ኔትብሎክስ ከዚህ በፊት ባወጣው ሪፖርት ገልጿል። ቲክቶክ፣ዩቲዩብ፣ቴሌግራም…
Read More
ኢትዮጵያ 500 ሺህ ሴቶችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ልትልክ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ 500 ሺህ ሴቶችን ወደ ሳውዲ አረቢያ ልትልክ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገር ልትልክ ነው በኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገራት በተለይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሥራ ለመላክ በመንግሥት እቅድ መያዙ ተገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም በአማራ ክልል ኹሉም ዞኖች ሰሞኑን ወደ አረብ አገር ሄደው መስራት ለሚፈልጉ ወጣት ሴቶች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ኢትዮ ነጋሪ ሰምታለች፡፡ ለአብነትም በምስራቅ ጎጃም ዞን ሦስት የስልጠና ማዕከላት የተዘጋጁ ሲሆን፣ በሞጣ፣ ደብረ ማርቆስ እና ደጀን ከተሞች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች የቤት አያያዝና ሌሎች አስፈላጊ የሥራ ስልጠናዎች እንደሚሰጡኢትዮ ነጋሪ ከዞኑ መረጃ አግኝታለች፡፡ ስልጠናው ለ20 ቀን በመንግሥት በነጻ የሚሰጥ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ ከስልጠናው በኋላ ፈቃደኛ የሆኑ ሴቶች ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚያቀኑበት የዚህ…
Read More
የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ አደገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በማደግ በኤሮስፔስ እና በተለያዩ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች በቅድመ ምረቃ እና ድሕረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተማር ጀመረ። የአቪዬሽን አካዳሚ የአቪዬሽን ስልጠና ፕሮግራሞችን በአብራሪነት፣ የአውሮፕላን ቴክኒሻን፣ የካቢን ሰራተኛ፣ የአየር መንገድ ሽያጭ እና አገልግሎት እና ሌሎች ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል።  ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካደገ በኋላ በኤሮኖቲካል ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአውሮፕላን ጥገና ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአቪዬሽን ማኔጅመንት ቢኤስሲ ዲግሪ፣ በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት ቢኤ ዲግሪ እና ኤምቢኤ በአቪዬሽን ማኔጅመንት የመሳሰሉ የዲግሪ መርሃ ግብሮችን ጀምሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት "ከቀጣይ እድገትና ኢንቨስትመንት በኋላ 65 ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ…
Read More
ዘምዘም ባንክ ከሀገር እና ውጭ ሀገራት ባንኮች ጋር ለመዋሃድ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ዘምዘም ባንክ ከሀገር እና ውጭ ሀገራት ባንኮች ጋር ለመዋሃድ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ዘምዘም ባንክ ከሀገር እና ውጭ ሀገራት ባንኮች ጋር ለመዋሃድ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ የኢትዮጵያ የባንክ ህግ መሻሻሉን ተከትሎ በቅርቡ ወደ አገልግሎት የገባው ዘምዘም ባንክ የተሻለ ገቢ እና ተወዳዳሪ ለመሆን ከሌሎች ባንኮች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ የባንክ ታሪክ ሙሉ ለሙሉ የእስላሚክ ባንክ አገልግሎትን በመስጠት ቀዳሚ የሆነው ዘምዘም ባንክ ከማንኛውም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ባንኮች ጋር ተዋህዶ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የባንኩ ፕሩዝዳንት ወይዘሮ መሊካ ለኢትዮ ነጋሪ በድሪ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ አክለውም ዘምዘም ባንክ ስራ ከጀመረበት ሰኔ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ54 ቅርንጫፎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ባንኩ ሙሉ ለሙሉ ወለድ አልባ የሆኑ ሁሉንም የፋይናንስ አገለግሎቶችን በመስጠት ላይ መሆኑን የተናገሩት…
Read More
የአንድ ኪሎ ሽንኩርት ዋጋ ከሥጋ ከሁለት እጥፍ በላይ የተወደደባት አገር

የአንድ ኪሎ ሽንኩርት ዋጋ ከሥጋ ከሁለት እጥፍ በላይ የተወደደባት አገር

ለምግብ ማጣፈጫነት ከሚውሉ አትክልቶች መካከል ሽንኩርት አንዱ ነው። ሽንኩርት በዓለም ዙሪያ መሠረታዊ የምግብ ግብአቶች ከሆኑት መካከል ይጠቀሳል። በበርካታ አገራት ሽንኩርት በድሃውም ሆነ በሃብታሙም ቤት የሚገኝ የምግብ አካል ሲሆን፣ ሥጋ ደግሞ እንደ ቅንጦት ምግብ የሚታይ ነው። በፊሊፒንስ ግን ይህ በተቃራኒ ሆኗል፤ የሽንኩርት ዋጋ የትኛውንም አይነት ሥጋ ለመግዛት ከሚወጣው ገንዘብ በበርካታ እጥፍ ይበልጣል። ለፊሊፒን ዜጎች ባለፉት ሳምንታት ጊዜ ሽንኩርት መሸመት ቅንጦት ሆኗል። ዋጋው በማሻቀቡ የተነሳ የሽንኩርት መግዣ ከሥጋ መግዣ በእጅጉ ንሯል። በዚህ ሳምንት ፊሊፒንስ ውስጥ አንድ ኪሎ ሽንኩርት 11 ዶላር (600 ብር ገደማ) ሲሆን፣ የአንድ ሙሉ ዶሮ ሥጋ ግን 4 ዶላር (220 ብር ገደማ) ብቻ ነው። የሽንኩርት ዋጋ ንረት የፈጠረውን የገበያ ክፍተት…
Read More
ሩሲያ በክሬሚያ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ላይ የደረሰዉ ፍንዳታ በሴራ ነዉ ስትል ተናገረች

ሩሲያ በክሬሚያ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ላይ የደረሰዉ ፍንዳታ በሴራ ነዉ ስትል ተናገረች

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰሜናዊ ክሬሚያ በሚገኝ ወታደራዊ መጋዘን የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ ከ3,000 በላይ ሰዎችን አካባቢዉን ለቀው እንዲወጡ ያስገደደ ሲሆን የሴራ ዉጤት ነዉ ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማስታወቁን የሩሲያ መንግስት ሚዲያ ዘግቧል። በትላንትናዉ እለት የደረሱት ፍንዳታዎች በሜይስኮዬ መንደር አቅራቢያ በሚገኘው የጥይት ማከማቻ ቦታን ያናወጡ እና የባቡር አገልግሎቶችን እንዲሁም የሃይል አቅርቦቶችን ያስተጓጎለ ነበር፡፡ በፍንዳታው በሰው ላይ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰ ሚኒስቴሩ አክሏል።የሩሲያ ኮምመርሰንት ጋዜጣ በትላንትናዉ እትሙ በክሬሚያ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ዘግቧል፡ እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው በግቫርዴስኮዬ ባሕረ ገብ መሬት ላይ በሚገኘው የሩሲያ ወታደራዊ አየር ማረፊያ ላይ ጭስ መታየቱን ጽፏል፡፡ባለፈው ሳምንት በክሬሚያ በሩሲያ ስር በሚተዳደረው የአየር ጣቢያ ላይ የደረሰ ፍንዳታ የነበረ ሲሆን ሞስኮ በወቅቱ…
Read More
የሮበርት ሙጋቤ ልጅ ድግስ ላይ ንብረት አውድሟል ተብሎ ታሠረ

የሮበርት ሙጋቤ ልጅ ድግስ ላይ ንብረት አውድሟል ተብሎ ታሠረ

የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ወንድ ልጅ ሃራሬ ውስጥ በተዘጋጀ ድግስ ላይ ንብረት አውድሟል ተብሎ በቁጥጥር ሥር ዋለ። 31 ዓመቱ እንደሆነ የሚገመተው ሮበርት ሙጋቤ ጁኒዬር ሶስት ንብረት የማውደም እና ሁለት ፖሊስ የመተናኮስ ክስ ቀርቦበታል ሲሉ ጠበቃቸው ተናግረዋል። በድግሱ ላይ የመኪናዎች መስታወት ሲረግፍ አንድ የፖሊስ መኮንን ላይ ምራቅ መተፋቱ ተሰምቷል። የሙጋቤ ልጅ የቀረበበትን ክስ አጣጥሎ ከደሙ ንፁሕ ነኝ ይላል። አሁን ከእሥር ተለቆ ክሱን በድርድር ለመፍታት እየጣረም እንደሆነ ተነግሯል። ፖሊስ በትዊተር ገፁ እንደገለጠው የሮበርት ሙጋቤ ልጅ ጓደኛ የሆነው ሲንዲሶ ንካታዞ ያቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ ነው ፖሊስ ወደ ሥፍራው ያቀናው። በድግሱ ላይ የደረሰው የንብረት ውድመት በገንዘብ ሲሰላ 12 ሺህ ዶላር አካባቢ ሊደርስ እንደሚችል ፖሊስ…
Read More