ዘምዘም ባንክ ከሀገር እና ውጭ ሀገራት ባንኮች ጋር ለመዋሃድ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

ዘምዘም ባንክ ከሀገር እና ውጭ ሀገራት ባንኮች ጋር ለመዋሃድ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ የባንክ ህግ መሻሻሉን ተከትሎ በቅርቡ ወደ አገልግሎት የገባው ዘምዘም ባንክ የተሻለ ገቢ እና ተወዳዳሪ ለመሆን ከሌሎች ባንኮች ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የባንክ ታሪክ ሙሉ ለሙሉ የእስላሚክ ባንክ አገልግሎትን በመስጠት ቀዳሚ የሆነው ዘምዘም ባንክ ከማንኛውም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ባንኮች ጋር ተዋህዶ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የባንኩ ፕሩዝዳንት ወይዘሮ መሊካ ለኢትዮ ነጋሪ በድሪ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ አክለውም ዘምዘም ባንክ ስራ ከጀመረበት ሰኔ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ54 ቅርንጫፎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ባንኩ ሙሉ ለሙሉ ወለድ አልባ የሆኑ ሁሉንም የፋይናንስ አገለግሎቶችን በመስጠት ላይ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ በተለይም ትኩረታቸውን በንግድ እና ኢንቨስትመንት ላይ ያደረጉ የሙዳረባ እና ሙራባሃ የተሰኙ አገልግሎቶችን በስፋት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሁለት ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ስራ የጀመረው ዘምዘም ባንክ አሁን ላይ የካፒታል መጠኑን ሶስት ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ 

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መስራት የሚያስችላቸውን ህግ ያወጣ ሲሆን የባንክ ባለሙያዎች የሀገር በቀል ባንኮች ተወዳዳሪ ለመሆን በመደራጀት እና በመወሃድ እንዲሰሩ ምክረ ሀሳብ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *