06
Mar
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ በማደግ በኤሮስፔስ እና በተለያዩ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፎች በቅድመ ምረቃ እና ድሕረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተማር ጀመረ። የአቪዬሽን አካዳሚ የአቪዬሽን ስልጠና ፕሮግራሞችን በአብራሪነት፣ የአውሮፕላን ቴክኒሻን፣ የካቢን ሰራተኛ፣ የአየር መንገድ ሽያጭ እና አገልግሎት እና ሌሎች ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካደገ በኋላ በኤሮኖቲካል ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአውሮፕላን ጥገና ኢንጂነሪንግ በቢኤስሲ ዲግሪ፣ በአቪዬሽን ማኔጅመንት ቢኤስሲ ዲግሪ፣ በቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ማኔጅመንት ቢኤ ዲግሪ እና ኤምቢኤ በአቪዬሽን ማኔጅመንት የመሳሰሉ የዲግሪ መርሃ ግብሮችን ጀምሯል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት "ከቀጣይ እድገትና ኢንቨስትመንት በኋላ 65 ዓመት ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉ…