ሩሲያ በክሬሚያ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ላይ የደረሰዉ ፍንዳታ በሴራ ነዉ ስትል ተናገረች

የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰሜናዊ ክሬሚያ በሚገኝ ወታደራዊ መጋዘን የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ ከ3,000 በላይ ሰዎችን አካባቢዉን ለቀው እንዲወጡ ያስገደደ ሲሆን የሴራ ዉጤት ነዉ ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማስታወቁን የሩሲያ መንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

በትላንትናዉ እለት የደረሱት ፍንዳታዎች በሜይስኮዬ መንደር አቅራቢያ በሚገኘው የጥይት ማከማቻ ቦታን ያናወጡ እና የባቡር አገልግሎቶችን እንዲሁም የሃይል አቅርቦቶችን ያስተጓጎለ ነበር፡፡

በፍንዳታው በሰው ላይ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰ ሚኒስቴሩ አክሏል።የሩሲያ ኮምመርሰንት ጋዜጣ በትላንትናዉ እትሙ በክሬሚያ ተጨማሪ ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ዘግቧል፡ እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው በግቫርዴስኮዬ ባሕረ ገብ መሬት ላይ በሚገኘው የሩሲያ ወታደራዊ አየር ማረፊያ ላይ ጭስ መታየቱን ጽፏል፡፡ባለፈው ሳምንት በክሬሚያ በሩሲያ ስር በሚተዳደረው የአየር ጣቢያ ላይ የደረሰ ፍንዳታ የነበረ ሲሆን ሞስኮ በወቅቱ ድንገተኛ አደጋ ነው ስትል መናገሯ ይታወሳል፡፡

በክሬሚያ ለደረሰው ፍንዳታ ዩክሬን በይፋ ሃላፊነቱን ከመዉሰድም ሆነ ፍንዳታዉን ከማስተባበል ተቆጥባለች፡፡ሩሲያ እ.ኤ.አ. በ2014 ከዩክሬን በህዝብ ዉሳኔ በጥቁር ባህር ላይ የምትገኘው የክሬሚያ ባሕረ ገብ መሬት ወደ ራሷ መጠቅለሏ ይታወሳል፡፡ዩክሬን ክሬሚያን ማስመለሴ አይቀርም ስትል ትዝታለች።

By New admin

4 thoughts on “ሩሲያ በክሬሚያ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ ላይ የደረሰዉ ፍንዳታ በሴራ ነዉ ስትል ተናገረች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *