ኢኮኖሚ

የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችዎቸን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስበው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡ በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን የሆነው "10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት(10th AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK  ASFW ) በአዲስ አበባ  ስካይ ላይት ሆቴል ከዛሬ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል። የፋሽን ሳምንቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስት አቶ መላኩ አለበል፣ ክብርት ሌንሳ መኮንን፣ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ እና ሌሎች በርካታ አንግዶች ከፍተውታል፡፡ ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን  ከተደረጉት ዝግጅቶች ሁሉ ትልቁ  ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የአፍሪካ ሶርሲንግና…
Read More
የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ባንኮች ወደ የኢትዮጵያ ለመግባት እያሰቡ ነው ተባለ

የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ባንኮች ወደ የኢትዮጵያ ለመግባት እያሰቡ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ እስካሁን በሯን ለውጭ ባንኮች ዝግ አድርጋ የቆየች ሲሆን አሁን ላይ የፖሊሲ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ የውጭ ሀገራት ባንኮች እንዲገቡ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በፊት መግለጹ ይታወሳል፡፡ ለዚህም ሲባል የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአንድ ዓመት በፊት የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ ለመግባት ከስድስት ወራት በፊት አመልክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የሞሮኮ፣ የኬንያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ባንኮች በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋ፡፡ ዋና ገዢው አክለውም የውጭ ሀገራት ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሰሩ የሚፈቅደው ህግ በቀጣዮቹ ሳምንታት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚጸድቅ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት የሚፈልጉ…
Read More
ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ዳታ ማይኒንግ ኩባያዎች 27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ዳታ ማይኒንግ ኩባያዎች 27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ለጎረቤት አገራት ከሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ከ31 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን አስታወቀ። ተቋሙ ለጅቡቲ ከሸጠው ከ169 ሺሕ 710 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል፣ 10 ሚሊዮን 379 ዶላር እና ለኬንያ ከሸጠው ከ314 ሺሕ 931 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል ከ20 ሚሊዮን 470 ሺሕ ዶላር ማግኘቱ ተገልጿል። በተመሳሳይ፣ ተቋሙ ለሱዳን ካቀረበው ከ13 ሺሕ 185 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ከ659 ሺሕ በላይ ዶላር ያገኘ ሲኾን፣ በሱዳኑ ጦርነት ሳቢያ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ለአገሪቱ ለማቅረብ ካቀደው ኃይል ውስጥ ያቀረበው 15 በመቶውን ብቻ እንደኾነ ተገልጧል። ኢትዮጵያ ውስጥ በዲጂታል መረጃ ማቀነባበር ከተሠማሩ የውጭ ኩባንያዎች በሩብ ዓመቱ ውስጥ ከተሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ደግሞ፣…
Read More
ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች 

ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች 

በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት ከወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል። ሚኒስትሩ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የወጪ ንግድ (ኤክስፖርት) አፈጻጸምን ከላኪዎች ጋር መገምገማቸውን አስታውቀዋል። አፈጻጸሙ በምርት ጭማሪም ሆነ በውጭ ምንዛሪ ዕድገት ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን አመላክተዋል። ይህም ከዕቅዱ 132 በመቶ መሳካቱንና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ አለው ተብሏል። በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን በማላቅ ኢኮኖሚው የሚፈልገውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ከዘርፉ ተዋናዮች እና ከላኪዎች ጋር የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም አመላክተዋል። ይህ በዚህ…
Read More
የአሜሪካው ቢትኮይን ክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ መሰማራቱን ገለጸ

የአሜሪካው ቢትኮይን ክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ መሰማራቱን ገለጸ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምናባዊ ገንዘብ ወይም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ፍላጎት እየጨመረ ሲሆን በኢትዮጵያም አጀንዳ ከሆነ አምስት ዓመት ሆኖታል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የትኛውንም ክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት እንዳልፈቀደ እና ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ ሰዎችም በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስታውቆ ነበር፡፡ ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በኢትዮጵያ የቢትኮይን ግብይት መፈጸም የሚያስችሉ መሰረተ ልማት ግንባታ የሚያደርጉ ኩባያዎች ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ አሁንም የክሪፕቶከረንሲ ግብይት እንዲደረግ ያልፈቀደች ሲሆን የዳታ ማዕከል ግንባታዎች እንዲካሄዱ ግን ስምምነቶችን በመፈራረም ላይ ነች፡፡ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የዎልስትሪቱ ቢትፉፉ የተሰኘው የክሪፕቶከረንሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ መሰማራት የሚያስችለውን ሂደት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ማካሄድ የሚያስችል የ80 ሜጋዋት ኤሌክትሪክ ሀይል መሰረት ልማት መግዛቱን ገልጿል፡፡ ቢትፉፉ የተሰኘው ይህ…
Read More
ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የ10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ የ10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

በኢትዮጵያና በኮሪያ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የ10 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል፡፡ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በኮሪያ ሪፐብሊክ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ መካከል የኢትዮጵያ የጥራት አመራር አቅም ማጎልበቻ ፐሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የግብርና እና የተቀናበሩ የግብርና ምርት ውጤቶች ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ላይ ያተኩራል የተባለ ሲሆን ለዚህም ደቡብ ኮሪያ ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ታደርጋለች ተብሏል፡፡ በፊርማ ስነስርዓቱ በኢትዮጵያ የኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሚስተር ሃን ዲዩግ ቾ እንደገለፁት የኢትዮጵያና የኮሪያ ሪፐብሊክ ግንኙነት ታረካዊ ነው ያሉ ሲሆን በኮሪያ ጦርነት ወቅት ከ6000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለኮሪያ ህዝብ ተዋግተው የደም ዋጋ የከፈሉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የፕሮጀክት ስምምነቱ የኮሪያ እና የኢትዮጵያ ወዳጅነትን…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቀረበ

ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቀረበ

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጩን በይፋ አስጀምሯል፡፡ 100 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ሀብት ያለው ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡ አንዱን የድርጅቱን አክስዮን ዋጋ በ300 ብር እንደሚሸጥ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም አንድ ግለሰብ መግዛት የሚችለው 33 አክስዮን ወይም 9 ሺህ 900 ብር ነው ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮ ቴሌኮም 3 ሺህ 333 አክስዮኖቹን ለሽጭ ያቀረበ ሲሆን 30 ቢሊዮን ብር ከአክስዮን ሽያጭ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች አክስዮን መግዛት ይችላሉ የተባለ ሲሆን ተቋማት ግን አክሲዮንን መግዛት እንደማይችሉ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡ የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃልም…
Read More
የኢትዮጵያ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫን እንዲያጠቡ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫን እንዲያጠቡ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ ግብይት ጋር በተያያዘ ስለሚፈጸሙ ክፍያዎች የማሻሻያ ፖሊሲ ይፋ አድርጓል:: ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህም ባንኮች በየእለቱ በሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ተመን ላይ በመግዣ እና በመሸጫው መካከል ከ10 በላይ ልዩነት ሲታይበት ቆይቷል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫው፤ አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል። በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት…
Read More
ሀይኒከን ኩባንያ አራዳ ቢራን ጠቀለለ

ሀይኒከን ኩባንያ አራዳ ቢራን ጠቀለለ

የአራዳ መጠጥ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ኮማሪ ቤቭሬጅ ለሃይኒከን መሸጡ ተገልጿል፡፡ በአጭር ጊዜ በተጠቃሚዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው የአራዳ መጠጦች አምራች ኮማሪ ፋብሪካውን ለሃይኒከን ለመሸጥ ሲያደርግ የነበረው ድርድር ከሳምንት በፊት አጠናቋል ተብሏል፡፡ የሽያጩ ድርድር ለበርካታ ወራት ሲደረግ ነበር የተባለ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በሀምሌ ወር ወደ መጨረሻ የድርድር ምእራፍ ቢሸጋገሩም ሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓም ወደ ትግበራ የገባውን የምንዛሬ ገበያ ለውጥ ተከትሎ ድርድሩ በድጋሚ ሲደረግ እንደነበር ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ የሽያጩ ዋጋ በዚህ ወር መጨረሻ በይፋ ይገለጻል የተባለ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በዚሁ ወቅት በይፋ ፋብሪካውን እንደሚረካከቡ ተገልጿል፡፡ ኮማሪ ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ 96 ኪሜ ርቀት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጨኬ አካባቢ በገነባው ፋብሪካ…
Read More
ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ መደበኛ የስልክ አገልግሎት ተቋረጠ

ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ መደበኛ የስልክ አገልግሎት ተቋረጠ

በ2010 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነበር ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለ20 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት ያደሱት፡፡ ሁለቱ ሀገራት የመደበኛ የስልክ አገልግሎትን ዳግም ካስጀመሩ ከሰባት ዓመታት በኋላ ተቋርጧል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ የስልክ አገልግሎት ሲሰራ የነበረ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ማለትም ከመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደተቋረጠ በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ኤርትራዊያን ሰምተናል፡፡ ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊ ለአል-ዐይን እንዳሉት “ከማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ ስልክ መደወል አልቻልኩም” ብለዋል፡፡ በኤርትራ ኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት ቤተሰቦቻችንን የምናገኘው በመደበኛ ስልክ ብቻ ነበር የሚሉት እኝህ አስተያየት ሰጩ አገልግሎቱ መቋረጡ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ “ቀስ በቀስ የኢትዮጵያ እና…
Read More