13
Oct
የአራዳ መጠጥ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ኮማሪ ቤቭሬጅ ለሃይኒከን መሸጡ ተገልጿል፡፡ በአጭር ጊዜ በተጠቃሚዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው የአራዳ መጠጦች አምራች ኮማሪ ፋብሪካውን ለሃይኒከን ለመሸጥ ሲያደርግ የነበረው ድርድር ከሳምንት በፊት አጠናቋል ተብሏል፡፡ የሽያጩ ድርድር ለበርካታ ወራት ሲደረግ ነበር የተባለ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በሀምሌ ወር ወደ መጨረሻ የድርድር ምእራፍ ቢሸጋገሩም ሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓም ወደ ትግበራ የገባውን የምንዛሬ ገበያ ለውጥ ተከትሎ ድርድሩ በድጋሚ ሲደረግ እንደነበር ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ የሽያጩ ዋጋ በዚህ ወር መጨረሻ በይፋ ይገለጻል የተባለ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በዚሁ ወቅት በይፋ ፋብሪካውን እንደሚረካከቡ ተገልጿል፡፡ ኮማሪ ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ 96 ኪሜ ርቀት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጨኬ አካባቢ በገነባው ፋብሪካ…