08
Nov
ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችዎቸን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስበው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡ በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን የሆነው "10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት(10th AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK ASFW ) በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ከዛሬ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል። የፋሽን ሳምንቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስት አቶ መላኩ አለበል፣ ክብርት ሌንሳ መኮንን፣ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ እና ሌሎች በርካታ አንግዶች ከፍተውታል፡፡ ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን ከተደረጉት ዝግጅቶች ሁሉ ትልቁ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የአፍሪካ ሶርሲንግና…