Blog

አማራ ባንክ ፕሬዝዳንቱን ከሀላፊነት አነሳ

አማራ ባንክ ፕሬዝዳንቱን ከሀላፊነት አነሳ

የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኄኖክ ከበደ ከሓላፊነታቸው ተነሱ የአማራ ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ፕሬዝዳንቱ አቶ ሔኖክ ከበደ ባንኩን ለ460 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ዳርገዋል በሚል ከሀላፊነት አንስቷል፡፡ ባንኩ ከዋና ሥራ አስፈጻሚው በተጨማሪም የኮርፖሬት አገልግሎት ዋና መኰንኑን አቶ ክንዴ አበበን፣ የአፈጻጸም ድክመት አሳይተዋል በሚል በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር  መላኩ ፈንታ ፊርማ ከሓላፊነታቸው አንሥቷል። የባንኩ ቦርድ ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ኹለቱም ከፍተኛ ሓላፊዎች፣ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ፣ በየጊዜው በሚሳዩት የሥራ አፈጻጸም ድክመት፣ የባንኩን ስትራቴጂያዊ ግቦች እና ቁልፍ የአፈጻጸም መመዘኛዎችን ማሳካት አልቻሉም ተብሏል፡፡ ባንኩ በ2014/15 ዓ.ም. ከ306 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ለማስመዝገብ ዐቅዶ የነበረ ቢኾንም፣ ብር 460,286,000 ኪሳራ አስመዝግቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በሌላቸው ሥልጣን ባሳለፉት አስተዳደራዊ…
Read More
ኢትዮጵያ በ50 ሚሊዮን ዶላር የትራክተር ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮጵያ በ50 ሚሊዮን ዶላር የትራክተር ፋብሪካ ልትገነባ መሆኗን ገለጸች

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሞጆ ከተማ በ50 ሚሊዮን ዶላር የትራክተር ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ተናግረዋል። ፋብሪካው ትራክተር የሚገጣጥም ሳይሆን ትራክተሩን ለማምረት የሚያስችሉ ዕቃዎችን የሚያመርት እራሱን የቻለ ፋብሪካ ይሆናልም ብለዋል። ተገዝተው በሚመጡ ትራክተሮች ብቻ የኢትዮጵያን ግብርና ማዘመን አይቻልም ያሉት አምባሳደር ሱሌይማን፤ ኢትዮጵያ የራሷን “ብራንድ” መትከል ስለሚገባት በሚሊዮን የሚቆጠር ትራክተር የሚያመርት ፋብሪካ መገንባት አለበት ብለን ወደ ተግባር በመግባት ላይ እንገኛለን ብለዋል። ፋብሪካው የትራክተር ሞተር ጭምር የሚያመርት ስለመሆኑ የጠቀሱ ሲሆን፤ ባሉን ፋብሪካዎችም የመኪና የውስጥ ክፍል “ሻንሲ” የመሥራት አቅም እያዳበርን በመሆኑ፤ ሞተር ማምረት ከቻልን መኪና የማምረት አቅም ላይ እንደሚደረስ ተናግረዋል፡፡ አሁን በመላ ሀገሪቱ በተጨባጭ ያሏት የትራክተሮች ቁጥር ከ100 ሺ…
Read More
ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ

ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ

የዓለማችን ስመ ገናናው የአቪዬሽን ተቋም ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ዳይሬክተር አድርጎ መሾሙን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው እንዳስታወቀው በፈረንሳይ የቀድሞ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሔኖክ ተፈራን የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አድርጎ እንደሾመ አስታውቋል፡፡ ቦይንግ አምባሳደር ሔኖክን የሾመው ኩባንያው ከአፍሪካ ጋር የሚኖረውን የንግድ እና ሌሎች ግንኙነት እንዲያሳልጡለት መሆኑን ገልጿል፡፡ አምባሳደር ሔኖክ አዲስ አበባ ሆነው ስራቸውን ያከናውናሉ የተባለ ሲሆን በቦይንግ የመካከለኛው ምስራቅ፣ ቱርክ እና አፍሪካ ፕሬዝዳንት ለሆኑት ኩልጂት ጋታ አውራ ጋር ይሰራሉ ተብሏል፡፡ ቦይንግ የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ እንደሚከፍት የገለጸ ሲሆን አምባሳደር ሔኖክ ደግሞ የኩባንያውን የአፍሪካ ስራዎች እንደሚመሩ አስታውቋል፡፡ አምባሳደር ሔኖክ በአቪዬሽን ንግድ ዘርፍ እና መንግስታዊ ግንኙነቶችን በመምራት ጥሩ ልምድ እንዳለቸው የገለጸው ቦይንግ በአፍሪካ…
Read More
በኦሮሚያ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 11 ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 11 ሰዎች ተገደሉ

በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ፣ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ እንደ ኢሰመኮ ሪፖርት ከሆነ በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ፤ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን፣ ኦዳ ብልድግሉ ወረዳ፤ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል፣ በአርሲ ዞን፣ ሸርካ ወረዳ እና በቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ወረዳ በሲቪል ሰዎች ላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በአማራ ክልል፣ በአዊ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር፣ በአየሁ ጓጉሳ ወረዳ፣ አምበላ ቀበሌ እና በዚገም ወረዳ ሶሪት ቀበሌ ከጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ…
Read More
ዳሸን ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎችን ሸለመ

ዳሸን ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎችን ሸለመ

ዳሸን ባንክ ባዘጋጀው ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፈው ያሸነፉ ተወዳዳሪዎችን ሸልሟል፡፡ ባንኩ ለውድድሩ አሸናፊዎች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጌያለሁ ያለ ሲሆን ለአሸናፊዎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር እስከ100 ሺህ ብር ሸልሟል። በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከነደፋቸው ትልልቅ መርሃ ግብሮች አንዱ ይህ የስራ ፈጠራ ውድድር መሆኑን ጠቁመው በመርሃ ግብሩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ስድስት ሺህ  ተወዳዳሪዎችን ማሳተፍና ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡ አቶ አስፋው ለውድድሩ አሸናፊዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉ ሲሆን ባንኩ ለወደፊት አብሯቸው እንደሚሰራና ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውም ቃል ገብተዋል፡፡ ለመጨረሻው ዙር የደረሱ ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው የተለያየ መጠን ያለው ሽልማት ያገኙ…
Read More
መንግሥት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ ጠየቀ

መንግሥት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ ጠየቀ

የኢትዮ ኒውስ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም የጸጥታ ክልሎች አራት ኪሎ በሚገኘው ከቢሮው አካባቢ እንዳሰሩት የስራ ባልደረባው እና ባለቤቱ ተናግረዋል። የጋዜጠኞች መሽት ተሟጋች የሆነው ሲፒጂ ባወጣው ሪፖርት ጋዜጠኛ በላይ ከታሰረ ሶስት ሳምንት እንዳለፈው እና እስካሁን ፍርድ ቤትም እንዳልቀረበ አስታውቋል። የሲፒጂ ሰብሰሀራ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ሙቶኪ ሙሞ እንዳሉት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የመስራት ነጻነታቸው መጎዳቱን ተናግረዋል ። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲለቅ ሲፒጂ አሳስቧል። እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የጋዜጠኞችን እስር እንዲያቆምም ሲፒጂ ጥሪ አቅርቧል። የጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ባለቤት በላይነሽ ንጋቱ ባለቤቷ አንድ ጊዜ ከታሰረበት ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ሄዳ እንደጠየቀችው የተናገረች ሲሆን በአማራ ክልል…
Read More
አይቴል ሞባይል አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ

አይቴል ሞባይል አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና ላለፉት አመታት ዘመናዊ እና ጥራት ያላቻውን የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በሚንቀሳቀስባቸው ለተለያዩ የአለም ገበያዎች ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የሚታወቀው አይቲል ሲጠቀምብት የነበረው የምርት አርማ እና መለዮ በአዲስ መልክ መቀየሩን አስታወቀ። በትራንሽን ማኑፋክችሪንግ ስር የሚንቀሳቀሰው አይቴል ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ሲሰራ የቆየውን አገልግሎት በአዲስ እና እጅጉኑ በተሻሻለ መለኩ ለማከናወን የሚያስችለው አዲስ የቢዝነስ እስትራቴጂ አንዱ አካል የሆነውን የምርት አርማ እና መለዮ የመቀየር ስራ በመጪው ጊዚ ለመተግበር የወጠናቸውን ልዩ ልዩ ስራዎች መሰረት እንደሚሆንም አሳውቆል።  አይቴል ይፋ ካደረገው አዲሱ አርማ እና መለዮ ለውጥ በተጨማሪ ኩባንያው በሚሰራባቸው እና ምርቱን ለገበያ በሚያቀርብባችው ሀገራት ውስጥ ሲተገብር የነበራቸውን የማህበረሰብ ተኮር ስራዎች…
Read More
በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ጠየቀ

በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ጠየቀ

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ማህበራዊ ፍትህ ለማስፈን በሚል ነበር ከ100 ዓመት በፊት ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት የተቀላቀለችው፡፡ ከአፍሪካ በብቸኝነት ድርጅቱን የተቀላቀለችው ኢትዮጵያ 100ኛ ዓመቱን በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመራሮች፣ አሰሪዎች፣ የሰራተኛ ማህበራት አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡ በዚህ በዓል ላይ ተገኝነተው ንግግር ያደረጉት ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ፋፋን ርዋንይንዶ ካይራንግዋ እንዳሉት ኢትዮጵያ ከ23ቱ የአይኤልኦ ስምንቶች መካከል ስምንቱን ማጽደቋን አድንቀዋል፡፡ ዳይሬክተሯ አክለውም ኢትዮጵያ የሰራተኞችን ደህንነት ለማሻሻል በርካታ የወሰደቻቸው እርምጃዎች ቢኖሩም ለሰራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ እርከን ጣሪያን እንድትወስን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንዳሉት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ድርጅት ከተቀላቀለች 100 ዓመት የሞላት…
Read More
መንግስት ብርን የማዳከም ፍላጎት እንደሌለው ገለጸ

መንግስት ብርን የማዳከም ፍላጎት እንደሌለው ገለጸ

ብሔራዊ ባንክ ሪፖርተር ጋዜጣ በሕዳር 23 እትሙ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ለማድረግ መታቀዱን በማስመልከት ያወጣው ዘገባ ሃሰተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡ የሪፖርተር የአማርኛ ጋዜጣ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ተመን ላይ በቅርብ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ ለማድረግ ማቀዱን በማስመልከት ያወጣው ዘገባ ፈጽሞ ሐሰተኛና አሳሳች፣ ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ያፈነገጠ ድርጊት መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡ ባንኩ ይህን አስመልክቶ  ባወጣው መግለጫ የሪፖርተር የአማርኛ ጋዜጣ በህዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም እትሙ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ከአንድ የፓርላማ አባል ቀረበ ከተባለ አስተያየት ላይ ተነሥቶ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ተመን ላይ…
Read More
የምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

የምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሊገነባ ነው፡፡ የንፋስ ሀይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ስምምነት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቱ አሜአ ፓወር ኩባንያ ጋር የስምምነት ፊርማ በዱባይ ተፈራርሟል፡፡ በሶማሌ ክልል አይሻ አካባቢ የሚገነባው የንፋስ ሀይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው እንደሆነ ተገልጿል። አጠቃላይ የንፋስ ሀይል ማመንጫው 600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት ሲሆን አሜአ ፓወር በተሰኘ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኩባንያ እንደሚገነባ ተጠቅሷል፡፡ ስምምነቱ በመንግስትና በግል አልሚዎች ማእቀፍ የሚሰራ ትልቁ ኢንቨስትመንት እንደሚሆን እንዲሁም በንፋስ ሀይል ማመንጫ ከምስራቅ አፍሪካ ግዝፉ ይሆናል ተብሏል። ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎቷን ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ሀይል…
Read More