07
Dec
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሞጆ ከተማ በ50 ሚሊዮን ዶላር የትራክተር ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ ተናግረዋል። ፋብሪካው ትራክተር የሚገጣጥም ሳይሆን ትራክተሩን ለማምረት የሚያስችሉ ዕቃዎችን የሚያመርት እራሱን የቻለ ፋብሪካ ይሆናልም ብለዋል። ተገዝተው በሚመጡ ትራክተሮች ብቻ የኢትዮጵያን ግብርና ማዘመን አይቻልም ያሉት አምባሳደር ሱሌይማን፤ ኢትዮጵያ የራሷን “ብራንድ” መትከል ስለሚገባት በሚሊዮን የሚቆጠር ትራክተር የሚያመርት ፋብሪካ መገንባት አለበት ብለን ወደ ተግባር በመግባት ላይ እንገኛለን ብለዋል። ፋብሪካው የትራክተር ሞተር ጭምር የሚያመርት ስለመሆኑ የጠቀሱ ሲሆን፤ ባሉን ፋብሪካዎችም የመኪና የውስጥ ክፍል “ሻንሲ” የመሥራት አቅም እያዳበርን በመሆኑ፤ ሞተር ማምረት ከቻልን መኪና የማምረት አቅም ላይ እንደሚደረስ ተናግረዋል፡፡ አሁን በመላ ሀገሪቱ በተጨባጭ ያሏት የትራክተሮች ቁጥር ከ100 ሺ…