Cop28UAE

የምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

የምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት 300 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የንፋስ ሀይል ማመንጫ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሊገነባ ነው፡፡ የንፋስ ሀይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ ስምምነት የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቱ አሜአ ፓወር ኩባንያ ጋር የስምምነት ፊርማ በዱባይ ተፈራርሟል፡፡ በሶማሌ ክልል አይሻ አካባቢ የሚገነባው የንፋስ ሀይል ማመንጫ 300 ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው እንደሆነ ተገልጿል። አጠቃላይ የንፋስ ሀይል ማመንጫው 600 ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚደረግበት ሲሆን አሜአ ፓወር በተሰኘ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ኩባንያ እንደሚገነባ ተጠቅሷል፡፡ ስምምነቱ በመንግስትና በግል አልሚዎች ማእቀፍ የሚሰራ ትልቁ ኢንቨስትመንት እንደሚሆን እንዲሁም በንፋስ ሀይል ማመንጫ ከምስራቅ አፍሪካ ግዝፉ ይሆናል ተብሏል። ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎቷን ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ሀይል…
Read More