10
Nov
በኢትዮጵያ በአጋቾች ታግቶ የቆየው ኬንያዊ ዜጋ 3 ሚሊየን ሽልንግ ከተከፈለ በኋላ መለቀቁን ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ። የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር እና በአዲስ አበባ ያሉት አምባሳደራቸው ባደረጉት ጥረት 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ ለአጋቾች ከተከፈለ በኋላ ሳሙኤል ንጃጊ የተባለው ዜጋቸው መለቀቁን ገልፀዋል። ሳሙኤል ከሳምንት በፊት በደብረ ብርሃን ከተማ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ድርጅት ታግቶ የተወሰደ ሲሆን የኬንያ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ካሳወቀ በኋላ ድርድሮች መደረጋቸው ተዘግቧል። ዊሊያም ሩቶ 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ በአጋቾች መጠየቁን ገልፀው ሳሙኤል ይሰራበት የነበረው ድርጅት ክፍያውን መክፈሉን ገልጸዋል። ሳሙኤል ከተለቀቀ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ መቆየቱንና ወደ ኬንያ ሄዶ ከቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀሉ ሲነገር ሩቶ ዜጎች…