02
Feb
በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአራት ወራት ተራዘመ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአማራ ክልል ባሳለፍነው ነሀሴ ለስድስት ወራት የታወጀው አስቸኳይ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት ተራዝሟል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በአማራ ክልል የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት አራዝሟል። የምክር ቤቱ አባላት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ አደረጉት በተባለው ውይይት ከዋጁ በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ለአራት ወራት እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ሚያዚያ ወር የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ ለማደራጀት ወስኛለሁ ማለቱን ተከትሎ ነበር በአማራ ክልል ግጭት የተከሰተው፡፡ ይህ ግጭት ቀስ በቀስ እያደገ መጥቶ ወደ ጦርነት የተቀየረ ሲሆን የቀድሞው የክልሉ መንግስት በመደበኛ…