Musafaki

ራይላ ኦዲንጋ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ ገለጹ

ራይላ ኦዲንጋ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ ገለጹ

ኬንያዊው ራይላ ኦዲንጋ የወቅቱ የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትን ለመተካት በሚደረገው ምርጫ ላይ መወዳደር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት የስልጣን ጊዜያቸው የፊታችን ሐምሌ ያበቃል፡፡ ይህን ተከትሎም ሙሳ ፋኪ መሀማትን ለመተካት ሀገራት ከወዲሁ እጩዎቻቸውን እያቀረቡ ሲሆን ኬንያዊው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል፡፡ ራይላ ኦዲንጋ ለዚህ እንዲረዳቸው የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ኦሊሶጎኖ ኦባሳንጆ ሀገራትን እንዲያሳምኑለት እንደመረጣቸውም ተናግሯል፡፡ የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በቀጣይ ግንቦት በሚደረገው ምርጫ ለማሸነፍ የተወሰኑ ሀገራትን ለማሳመን ጥረት መጀመራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ይሁንና ራይላ ኦዲንጋ…
Read More