Samoaagreement

ኢትዮጵያ የሳሞአ ስምምነትን እንድትሰርዝ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ

ኢትዮጵያ የሳሞአ ስምምነትን እንድትሰርዝ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንዳስታወቀው ኢትዮጵያ በአውሮፓ ኅብረት፣ አፍሪካ፣ ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነትን ውድቅ እንድታደርግ ጠይቋል፡፡ ተቋሙ ይህ ስምምነት የተጠቀሰው የወሲብና የስነ ተዋልዶ ጤና እና መብቶች በሚል ዘርፍ የተደረገው ስምምነት ከግብረሰዶም መብቶች፤ ከፆታ መቀየር፤ ከጽንስ ማቋረጥ እንዲሁም የወሲብ ንግድን የሚያበረታታ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በስምምነቱ የአፍሪካ ፕሮቶኮል አንቀፅ 40.6 ላይ በአህጉሪቱ ለሚገኙ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት የተባለ እጅግ አደገኛ ልቅ የወሲብ ትምህርት እንዲማሩ የሚያስገድድ በመሆኑ እንደሚቃወመውም ገልጿል፡፡ ሌላኛው ተቋሙ የተቃወመው የፆታ ትንኮሳን ማስቀረት በሚል የተቀመጠው ይዘት በጣም አሻሚ የሆነ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ እንዲረዳው በሰነዱ በበርካታ ክፍሎች ውስጥ " አካታች "…
Read More