08
Feb
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አዳዲስ ሹመቶችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አጸድቀዋል፡፡ በዚህም መሰረት የብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀድሞ አምባሳደር የነበሩት ታዬ አጽቀስላሴ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡ እንዲሁም ዶክተር መቅደስ ዳባ ደግሞ ከጤና ሚኒስትርነት ሀላፊነታቸው የመልቀቂያ ደብዳቤ ላሰገቡት ዶክተር ሊያ ታደሰ ምትክ ሆነው ተሾመዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደህንነት አማካሪ የነበሩት ሬድዋን ሁሴን ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይረክተር ተሹመዋል። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሆነው ከመስራታቸው በፊት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኢታ፣በኤርትራ እና አየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና…