Droneattack

ኢህአፓ መንግስት በሚፈጽማቸው የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎችን እየገደለ ነው ሲል ከሰሰ

ኢህአፓ መንግስት በሚፈጽማቸው የድሮን ጥቃቶች ሰላማዊ ዜጎችን እየገደለ ነው ሲል ከሰሰ

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ “የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት መንግሥት ቢሆንም በሚያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጭምር የዜጎች ህይወት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች እንደቅጠል እያረገፈ ይገኛል” ብሏል፡፡ ኢሕአፓ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ህገመንግሥቱን የመንግሥት አካላት ራሳቸው ካላከበሩት እንዴት ሊያስከብሩት ይችላሉ “በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚደረጉት ግድያዎች ይቁሙ” ሲል አሳስቧል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ከመዘገብ ቢቆጠቡም በውጪ የመገናኛ ብዙሀን ጭምር ጥቃቱ መፈጸሙን እየገለጹ መሆኑን እና ፓርቲውም አጣርቻለሁ ያለውን በየክልሉ የደረሱትን ጥቃቶች አስታውቋል፡፡ ፓርቲው አጣርቻለው ባለው መሰረት ኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች የሟቾችን ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን እና ጥቃት ከተፈጸመባቸው ውስጥም ነፍሰጡሮች፣ የጤና ባለሙያዎች እና በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች እንደሚገኙበት…
Read More
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ተገደሉ

አንድ ዓመት ባስቆጠረው የአማራ ክልል የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ግጭት መቋጫ አላገኘም፡፡ በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጉሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የተሬ ቀበሌ ነዋሪ እንዳለው “ትናንት ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በመንደራችን ከባድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ እኔን ጨምሮ የሰፈራችን ነዋሪዎች ፍንዳታው ወደ ተሰማበት ስፍራ ስንሄድ ጥቃቱ ጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደተፈጸመ አየን” ሲል ተናግሯል፡፡ አስተያየት ሰጪው አክሎም “በዚህ የድሮን ጥቃት ሶስት አርሶ አደሮች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት…
Read More
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 30 ንጹሃን ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 30 ንጹሃን ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃ እና ወደራ ወረዳ ሳሲት በተባለች ከተማ ህዝብ ያሳፈረ አይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመው ጥቃት 30 ሰዎች ሲገደሉ 18 ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ከአምስት ቀን በፊት ሳሲት በተባለችው ከተማ አቅራቢያ 50 ሰዎችን ያሳፈረ አይሱዙ ተሽከርካሪ መንገደኞችን ለማውረድ በቆመበት ተፈጽሟል በተባለው ጥቃት 18 ሰዎች መቁሰላቸውንም ነው የአይን እማኞችን የጠቀሰው የሪሊፍ ዌብ ዘገባ የሚያሳየው። የድሮን ጥቃቱ ሲፈጸም በአካባቢው በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት እንዳልነበር የተናገሩት ነዋሪዎች፥ ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላም ድሮኖች በአካባቢው ሲሽከርከሩ እንደነበር ገልጸዋል። የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው መከላከያ ሰራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች ውጊያ ከሚያደርጉበት አካባቢ በ24 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደተፈጸመ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ “መጀመሪያ ከባድ ፍንዳታ ሰማን ከዚያም…
Read More