22
Feb
አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ ባለመኖሩ የሆቴሎች ገቢ እየቀነሰ መሆኑን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር እስታወቀ። ተደራራቢ ችግር እንደፈተነው የሚነገረው የሆቴል ስራ አገልግሎት አሁን ደግሞ የተረጋጋ ሰላም ባለመኖሩ ከአገልግሎቱ እየወጡ የሚገኙ ድርጅቶች መኖራቸው ታውቋል። የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ወይዘሮ አስቴር ሰለሞን ኮቪድ19 ካደረሰው ጉዳት ያላገገሙ ሆቴሎች አሁን ደግሞ በፀጥታ ችግር ምክንያት ከውጭ የሚገቡ ደንበኞቻቸውን እንደልብ ማግኘት አልቻሉም ብለዋል። ለተከታታይ ዓመታት የዘለቀው የፀጥታ ችግር አሁንም መቀጠሉ በኮከብ ደረጃ ያሉ ሆቴሎች ገቢያቸውን በሀገር ውስጥ ደንበኞች ብቻ መሸፈን አዳጋች እንዳደረገባቸውም ገልፀዋል። በኮቪድ 19 ወቅት ሆቴሎች ሰራተኞችን እንዳይበትኑና ለአንዳንድ ወጪዎች እስከ 5 በመቶ የወለድ ምጣኔ ብድር ማግኘታቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቷ፥ አሁን ላይ ይህ ድጋፍ መቅረቱን…