Oilseeds

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላከ ቅባት እና ጥራጥሬ እህሎች 285 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት ከተላከ ቅባት እና ጥራጥሬ እህሎች 285 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ባለፉት ስድስት ወራት ከቅባትና ጥራጥሬ እህሎች የወጪ ንግድ 285 ነጥብ 53 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከቅባት እህሎች የወጪንግድ 109 ነጥብ 66ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን አፈጻጸሙም 109 በመቶ መሆኑን ሚኒሰቴሩ በስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርቱ ገልጿል፡፡ ይህም ካምናው ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ26 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ በስድስት ወራቱ በጥራጥሬ እህል የተገኘው ገቢ 176 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ77 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ከቅባትና ጥራጥሬ እህሎች የወጪ ንግድ በድምሩ 285 ነጥብ 53 ሚሊየን የአሜሪካን…
Read More