Mauritania

ማውሪታኒያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን ከኮሞሮስ ተረከበች።

ማውሪታኒያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን ከኮሞሮስ ተረከበች።

37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ሲሆን የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ማውሪታኒያ በ2024 የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት እንድትመራ የተመረጠች ሲሆን የሊቀመንበርነት ቦታውን ከ2023 የህብረቱ ሊቀመንበር ከነበረችው ኮሞሮስ ተረክባለች፡፡ የማውሪታኒያ ፕሬዝደንት መሀመድ ኦዉልድ ጋዞኒ ከወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር ከኮሞሮሱ ፕሬዝደንት አዛሊ አሶውማኒ ተረክበዋል። የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት ስልጣን የህብረቱ አባል ሀገራት በየዓመቱ እየተቀያየሩ የሚያገኙት ስልጣን ሲሆን ከህብረቱ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር በመሆን ስራን ማቀላጠፍ እንዲሁም አፍሪካን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የመሳተፍ ሀላፊነት አለበት፡፡ ፕሬዝደንት ኦውልድ ዛሬ የተመረጡት የህብረቱ ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት የሆነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ረብዕ እና ሐሙስ ዕለት ባካሄዱት ጉባኤ እንዲመረጡ ይሁንታ ከሰጣቸው…
Read More