Ethiopiapremierleague

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሊመለስ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ4 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሊመለስ ነው

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2016 እግር ኳስ ውድድር የጨዋታ ፕሮግራም ባሳለፍነው ነሀሴ ከወጣ በኋላ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታን ባለሜዳው አዳማ ከነማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል ተደርጎም ነበር፡፡ የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ላለፉት አራት ዓመታት በአዳማ፣ ድሬዳዋ፣ሐዋሳ እና ባህርዳር ስታዲየሞች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የፕሪሚየር ሊግ እና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን ወደ ክልል ከተሞች እንዲዞሩ የግድ ሆኖ ቆይቶም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ እንደገለጸው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻዎቹ ሶስት ሳምንታት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደረግ ገልጿል። የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መርሃ ግብርና የውድድር ሜዳዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም በስታዲየሞች…
Read More