AddisAbaba

በአማራ ክልል ያለው ስደት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

በአማራ ክልል ያለው ስደት አስደንጋጭ መሆኑ ተገለጸ

የአማራ ክልልን ለቆ ወደ ስደት እና ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚፈልሰው የክልል ተወላጅ መጠን "አጅግ አስደንጋጭ " መሆኑን የክልሉ ምክር ቤት አባላት ተናገሩ። በአማራ ክልል ባለፉት 5 ወራት ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች 36 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል። ይህ የተነገረው የትምህርት ቢሮው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ የ5 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት እንደሆነ ሸገር ኤፍኤም ዘግቧል። የምክር ቤቱ አባላት ለተማሪዎች በትምህርት ገበታ አለመገኘት ጦርነቱን፣ ስደት፣ የቀን ስራ፣ በትምህርት ተስፋ መቁረጥን ጨምሮ የተለያዩ ምክንያቶችን ዘርዝረዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ወደ ትምህርት ያልተመለሱ ተማሪዎች አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንኳን መረጃ ማግኘት እንዳልተቻለ አስረድተዋል። አንድ የምክር…
Read More
ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በ38 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በ38 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

​የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የጥቅምት 2025 ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት የድንበር ፍሰት መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ የታየው የሰዎች እንቅስቃሴ ካለፈው መስከረም ወር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል። በወሩ ውስጥ በአጠቃላይ 45,150 የሰዎች ዝውውር የተመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በቀን በአማካይ 1,456 ሰዎች ድንበር እንደሚያቋርጡ ያሳያል ነው የተባለው። ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አብዛኛው ማለትም 78.3 በመቶው (35,341 ሰዎች) ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ የሚወጡ ሲሆን፣ ቀሪው 21.7 በመቶው (9,809 ሰዎች) ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ናቸው። በጥቅምት ወር ድንበር አቋርጠው የሚወጡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ካለፈው የመስከረም ጋር ሲነጻጸር የ38 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሪፖርቱ አመላክቷል። ይህ የፍልሰት መጨመር በተለይ በሱዳን ድንበር በሚገኘው በመተማ በኩል በከፍተኛ ሁኔታ የታየ…
Read More
በጋምቤላ ክልል እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ኢሰመኮ አሳሰበ

በጋምቤላ ክልል እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ኢሰመኮ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከኅዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ (አቦል)፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ሥጋቶችን እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል። ኢሰመኮ ባሰባሰበው መረጃ በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡመድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በከተማውና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎችና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ መቆየቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም ሳቢያ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የሰዎችን እና የመጓጓዣ አማራጮችን እንቅስቃሴ የሚገድብ የሰዓት እላፊ በክልሉ መንግሥት መጣሉን፤ ባንኮችንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት…
Read More
በጋምቤላ ክልል የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ

በጋምቤላ ክልል የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ

የጋምቤላ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ "ግጭት እና የሰው ሞት የሚያስደስታቸው ሀይሎች በሰሞኑ የጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎች ትርምስ ፈጥረዋል" ብሏል። የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር ተባብሮ ያመጣውን ሰላም እና ልማት ወደ ኋላ ለመመለስ እየሰሩ ያሉ እነዚህ በእኩይ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ሀይሎች በየቦታው ሰዎችን በመግደል፣ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት በማድረስ እና ህይወት እንዲጠፋ በማድረግ፣ የፀጥታ አካላትን እና አመራርን ኢላማ በማድረግ ወደ ለየለት የሕዝቦች እልቂት ለማስገባት የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነም ክልሉ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል። የክልሉ መንግሥት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ተጠርጣሪዎችን አድኖ በህግ ቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነም ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት አሁን ላይ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ስራዎችን…
Read More
ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

ኢትዮጵያ ሁሉንም የስፖርት ውርርድ ቤቶች ፈቃድ ሰረዘች

በኢትዮጵያ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃድ መሰረዙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሁሉንም የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች የሥራ ፈቃዶች ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሰረዛቸውን ገልጿል። የፈቃድ ስረዛው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፉ ላይ በተካሄደ አገር አቀፍ ጥልቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ውሳኔው በስራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ የተንሰራፋ ሀገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆኑ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውሮች እንዳሉ በግልጽ አመላክቷል። ለስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም…
Read More
ኤርትራ ከኢጋድ ለመልቀቅ ያሳለፈችውን ውሳኔ ዳግም እንድታጤነው ተጠየቀች

ኤርትራ ከኢጋድ ለመልቀቅ ያሳለፈችውን ውሳኔ ዳግም እንድታጤነው ተጠየቀች

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ፤ የኤርትራ መንግሥት ከድርጅቱ የመውጣት ውሳኔ ያሳለፈው “ተጨባጭ ሃሳቦች ወይም በአይነተኛ ተቋማዊ ወይም የፖሊሲ ማሻሻያዎች ዙሪያ ተሳትፎ” ሳያቀርብ መሆኑን በማንሳት ቅሬታውን ገልጿል። ኢጋድ ይህንን ውሳኔ በይፋዊ የቃል ማስታወሻ መግባቱን አረጋግጧል። ሆኖም ግን፣ ሴክሬታሪያቱ ለድርጅቱ የተላከው ማስታወሻ ከማንኛውም ቀደም ያለ ውይይት ውጪ መሆኑን ጠቁሟል። ኤርትራ ለሁለት አሥርት ዓመታት ያህል በራሷ ፍላጎት አባልነቷን ካገደች በኋላ፣ እ.ኤ.አ. ሰኔ 2023 በተካሄደው 14ኛው የልዩ መሪዎች ጉባኤ ላይ በሁሉም አባል አገሮች በሞቃት አቀባበል ወደ ድርጅቱ ተመልሳ ነበር ብሏል። በዚያን ወቅት፣ መመለሷ “ሁሉን አቀፍነት፣ የክልላዊ ወንድማማችነት እና የታደሰ ትብብር የጋራ ቁርጠኝነት” ማሳያ እንደነበር ድርጅቱ አስታውሷል። ነገር ግን፣ ኢጋድ ከሰኔ 2023…
Read More
የቀድሞው ጉምቱ ባለስልጣን የ13 ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የቀድሞው ጉምቱ ባለስልጣን የ13 ዓመት እስር ተፈረደባቸው

የቀድሞው የአደጋ ስጋት ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በከባድ የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል። የፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ፣ አቶ ምትኩ ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር በመሆን የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ከ601 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴን ጨምሮ በርካታ የምግብ እርዳታ ቁሳቁሶችን ከመጋዘን በማውጣት ለተረጂዎች ሳይደርስ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉ አስረድቷል። በተጨማሪም፣ ከ472 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲከፈል በማድረግ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ…
Read More
በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

በኢትዮጵያ ዓመታዊ የድጅታል ገንዘብ ልውውጥ ከ18 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ብሔራዊ ባንክ እንዳስታወቀው በአንድ አመት ውስጥ በጂታል ክፍያ ስርአት 18 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ዝውውር ተፈጽሟል። በኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ኮንፈረንስ 2.0. ላይ ለአምስት አመት የሚቆይ (2026-30) የብሔራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ በብሔራዊ ባንክ ይፋ ሆኗል። የመጀመሪያው የ2021-24 ብሄራዊ የዲጂታል ክፍያ ስትራቴጂ ላይ ህግ ማውጣት፣ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ማስቻልና ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወናቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ስርአት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ዳምጠው ለቅዳሜ ገበያ እንደገለጹት በኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ትልቁ ሚና የገንዘብ ዝውውር ፈጣን ቀልጣፋ ወጪ ቆጣቢ መሆን አለበት። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የዲጂታል የክፍያ ስርአትን ማዘመን እና ለዚያ የሚያበቃ የድጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ባለፈው አንድ አመት…
Read More
የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት ሀገራትን እንደሚጎበኙ አስታውቀዋል። እንደ ኢንዲያ ቱዴይ ዘገባ ከሆነ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ከታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ፣ ጆርዳን እና ኦማንን ይጎበኛሉ። ኢትዮጵያ እና ሕንድ ጥሩ ወዳጅነት ያላቸው ሲሆን ከ15 ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ሞንማሆን ሲንግ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ-ሕንድ ቢዝነስ ጉባኤ ላይ ተሳትፈው መመለሳቸው ይታወሳል። ሁለቱ ሀገራት ረጅም እድሜ ያስቆጠረ የዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ያላቸው ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ውስጥ ተሳትፈዋል። የብሪክስ አባል የሆኑት ኢትዮጵያ እና ሕንድ በትምህርት ፣ ጤና፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ዙሪያ በመተባበር ላይ ናቸው ተብሏል። ሕንድ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ነጻ የትምህርት እድል በስፋት ከሚሰጡ ሀገራት…
Read More
ያንጎ  በኢትዮጵያ መተገበሪያው ላይ አዲስ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ ማከሉን ገለጸ

ያንጎ  በኢትዮጵያ መተገበሪያው ላይ አዲስ የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ ማከሉን ገለጸ

የአለምዓቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ራይድ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያገለግለው መተግበሪያው ውስጥ የሚገኘውን የደንበኛ ደህንነት መጠበቂያ አሻሽያለሁ ብሏል። ተሻሻለው መተግበርያ እያንዳንዱ ተጓዥ ዝርዝር የደህንነት መስፈርቶች መሟላታቸውን የሚያረጋግጥበት አገግሎግሎት፥ በወቅታዊ የጉዞ ሁኔታ መረጃ ላይ ተመስርቶ ምን አይነት የደህንነት እርምጃዎች መወሰድ እንደሚገቡ መረጃ የሚሰጥ እንዲሁም ስለ ጉዞ ደህንነት አጠቃላይ የደህንነት መረጃዎች የሚሰጥ የማዕከል አገልግሎት የተካተተበት ነው ተብሏል።አዲሱ የደህንነት ማዕከል የመተግበሪያውን አጠቃቀም ማንበብ፣ የግል መረጃን መሙላት ፣ የሚያምኗቸውን ሰዎች ስልክ ቁጥር መሙላት፣ የራስን ፎቶ ማንሳት እና ኢ-ሜል መቀየርን የመሳሰሉ ተሳፋሪዎች መሙላት ያለባቸውን ዝርዝሮችም ይይዛል።ከዝርዝሩ ውስጥ የጎደለ ነገር ካለ መተግበሪያው ያልተሞላው ላይ ምልክት በማድረግ ተሳፋሪው እንዲሞላው ይጠይቃል። ተሳፋሪዎች የአጋር አሽከርካሪዎችን ስታንዳርድ፣ አደጋ…
Read More