29
Jan
የታሸገ ውሃ አምራቾች በሦስት ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የታሸገ ውሃ አምራቾች ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ መወሰናቸውን ገልጸዋል። አዲስ በሚጠበቀው የታሸገ ውሃ የማከፋፈያ ዋጋ ጭማሪ በሁለት ሊትር ውሃ ላይ እስከ 20 በመቶ ይደረጋል የተባለ ሲሆን ይህም በሶት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የውሃ አምራቾቹ በኅዳር ወር በተመሳሳይ የ22.5 በመቶ ጭማሪ አድርገው የነበረ ሲሆን በወቅቱ ለዋጋ ማስተካከያው ምክንያት ነው የተባለው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እና ሌሎች ግብአቶች ወጪያቸው ጨምሯል በሚል ነበር። በቀጣይ ሳምንት ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው ጭማሪ ምክንያታዊነቱ ላይ ጥያቄ ያስነሳል የተባለ ሲሆን የዋጋ ጭማሪው በተጠቃሚዎች እና አከፋፋዮች ላይ እክል ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል ሲል…