16
Jan
የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዘመናዊ የሆነውን የመጀመሪያ ዙር የsu-30 ተዋጊ ጀቶችንና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖች መረከቡን ተገለጸ። በርክክቡ ላይ የተገኙት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፤ በዓለማችን ላይ ተመራጭ የሆኑትን የsu-30 እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላን ባለቤት መሆናችን በሀገራችን ላይ ሊቃጡ የሚሞከሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል። የ5ኛ ትውልድ አካል የሆኑት ዘመናዊ ተዋጊ አውሮፕላኖችና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕላኖች አየር ሀይሉን የማዘመን አንዱ አካል መሆናቸውንም ጠቁመዋል። የኢትዮጵያን የአየር ክልል ከማንኛውም ጥቃት ሊከላከሉ የሚችሉ ዘመናዊ የውጊያ ትጥቆችን የመታጠቅ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኤታማዦር ሹሙ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር ሀይል "በአፍሪካ በውጊያ አቅሙ፣ በጀግንነቱና በትጥቁ የነበረውን ዝና ዘመኑ በሚጠይቀው መልኩ ለማዘመን"…