Coalmining

በኢትዮጵያ ግዙፉ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ

በኢትዮጵያ ግዙፉ የድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ፋብሪካ በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል። የከሰል ማዕድን አምራቹ ኢቲ ማይኒንግ ፋብሪካ እንደሚሰኝ ሲገለፅ ፋብሪካው 150 ቶን ከሰል በሰዓት የማምረት አቅምና የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን 75 በመቶ የድንጋይ ከሰል ፍላጎት ለማሟላት ያስችላል ተብሏል። የፋብሪካው ፕሮጀክት ማናጀር ኢንጅነር በላይ አሰፋ የኢትዮጵያ የታጠበ ከሰል ፍላጎት ሀገሪቱ በዓመቱ በአማካይ 400 ሚሊዮን ዶላር እያሳጣት መሆኑን ገልፀዋል። ይህ ፋብሪካ ከሁለት ዓመት በፊት ተጀምሮ በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ ሥራው እየተጠናቀቀ በመሆኑ በፋብሪካው የሚሠሩ ቋሚ ሠራተኞች ሥልጠና እየተሰጠና የሙከራ ሥራዎች ከተሠሩ በኋላ ከሁለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተመርቆ ሥራ ይጀምራል ተብሏል።…
Read More