16
Dec
የኢትዮጵያ አየር ሀይል የተመሰረተበትን 88ኛ ዓመት በማክበር ላይ ስትሆን በዛሬው ዕለት ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የጦር ጄቶች ጋር በመሆን የአየር ላይ ትርዒት አድርገዋል፡፡ በአዲስ አበባ በተካሄደው በዚህ የጦር አውሮፕላኖች ትርዒት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የጦር አውሮፕላኖች ያካሄዱት የአየር ላይ ትርዒት “የጥቁር አንበሳ የአየር ትርዒት” የሚል ስያሜ እንደተሰጠው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል፡፡ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ወታደራዊ አታሼዎች ባሳለፍነው ሳምንት ቢሾፍቱ የሚገኘውን የኢትዮጵያን አየር ሀይል ዋና ማዘዣን የጎበኙ ሲሆን በዛሬው በዓል ላይም ተገኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ1928 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በአፍሪካ ካሉ አየር ሀይሎች በእድሜ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ትርዒቶችን በአደባባይ ላይ ማክበር እየጨመረ የመጣ…