13
Dec
ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር በየጊዜው ለሽፓጭ ከሚያውላቸው የእድል ሎተሪዎች መካከል የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንዱ ነው። 20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ይህ እጣ ባሳለፍነው ጷግሜ 2015 ዓም እጣው የወጣ ሲሆን 1820259 ደግሞ የመጀመሪያ እድለኛ ቁጥር እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል። የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ንዋይ ለዓልዐይን እንዳሉት "ባሳለፍነው ጷግሜ ላይ ከወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከሶስት እጣ አሸናፊ በስተቀር የሁለት እጣ አሸናፊዎች እስካሁን አልመጡም" ብለዋል። ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድሩ የሁለት እጣ እድለኞች ማለትም የስምንት ሚሊዮን ብር አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ካልመጡ ገንዘቡ ለመንግሥት ገቢ ይሆናልም ብለዋል። 20 ሚሊዮን ብር ከሚያሸልመው እጣ ቁጥር ውስጥ እስካሁን በመተሀራ ከተማ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በወዛደርነት…