NationalLottery

ብሔራዊ ሎተሪ የ8 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እድለኛ እንደጠፋበት ገለጸ

ብሔራዊ ሎተሪ የ8 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እድለኛ እንደጠፋበት ገለጸ

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር በየጊዜው ለሽፓጭ ከሚያውላቸው የእድል ሎተሪዎች መካከል የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንዱ ነው። 20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ይህ እጣ ባሳለፍነው ጷግሜ 2015 ዓም እጣው የወጣ ሲሆን 1820259 ደግሞ የመጀመሪያ እድለኛ ቁጥር እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል። የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ንዋይ ለዓልዐይን እንዳሉት "ባሳለፍነው ጷግሜ ላይ ከወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከሶስት እጣ አሸናፊ በስተቀር የሁለት እጣ አሸናፊዎች እስካሁን አልመጡም" ብለዋል። ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድሩ የሁለት እጣ እድለኞች ማለትም የስምንት ሚሊዮን ብር አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ካልመጡ ገንዘቡ ለመንግሥት ገቢ ይሆናልም ብለዋል። 20 ሚሊዮን ብር ከሚያሸልመው እጣ ቁጥር ውስጥ እስካሁን በመተሀራ ከተማ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በወዛደርነት…
Read More
የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ሽልማት ወደ አራት ሚሊዮን አደገ

የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ሽልማት ወደ አራት ሚሊዮን አደገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በቅርቡ የጀመረው አድማስ ድጅታል ሎተሪ የሽልማት መጠኑን ማሳደጉን ገልጿል፡፡ አድማስ ድጅታል ሎተሪ ከመስከረም 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአንደኛ አሸናፊ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በመሸለም ነበር የጀመረው፡፡ በመቀጠልም የሽልማት መጠኑን ወደ ሶስት ሚሊዮን ብር ከፍ የተደረገው አድማስ ድጅታል ሎተሪ ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም በሶስት ብር እና በአምስት ብር የሎተሪ እጣ የሚቆርጡበት የሎተሪ ስርዓት ነው፡፡ በደምበኞች አስተያየት መሰረት ቀደም ሲል የነበበረውን የዕጣ ሽልማት የአንደኛው ዕጣ 4 ሚሊዮን ብር፣ የሁለተኛው ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር የሶስተኛው ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር በማድረግ ተደርጓል ተብሏል፡፡ እንዲሁም ደንበኞች ከሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አንድ እጣ በ10 ብር በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ…
Read More
ለ15ኛ ጊዜ ሎተሪ የደረሳቸው የጎንደሩ እድለኛ አባት

ለ15ኛ ጊዜ ሎተሪ የደረሳቸው የጎንደሩ እድለኛ አባት

ግለሰቡ በአንድ ዓመት ውስጥ የገናን እና ፋሲካ በዓል ሎተሪን አሸንፈዋል አቶ መሃመድ አህመድ አህመድ ይባላሉ፤ተወልደው ያደጉት ጎንደር ነው፡፡ አቶ መሃመድ ሙሉ ስማቸው መሃመድ አህመድ ቢሆንም በተደጋጋሚ ሎተሪ ስለጎበኛቸው የአባታቸው ስም ወደ ሎተሪ ተቀይሮ በሚኖሩበት ከተማ መሃመድ ሎተሪ እየተባሉ በመጠራት ላይ ናቸው፡፡ አቶ መሃመድ ሎተሪ 15 ጊዜ የሎተሪ እድል አሸናፊ መሆናቸውን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር መረጃ ያመላከታል፡፡ ከ1977 አመት ጀምሮ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ሎተሪ ቆርጠው ያጡት ብር እንደሌለ እኝህ አባት ይናገራሉ፡፡ አቶ መሃመድ ከ500 ብር ጀምሮ እስከ 75ሺህ ብር ድረስ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ የእኝህ አባት እድለኝነት የሚያስገርመው ደግሞ የገና ሎተሪ እጣ አሸናፊ ሆነው በዛው አመት በፋሲካም አሸናፊ መሆናቸው ነው፡፡ በሎተሪ ተስፋ ቆርጠው…
Read More