ዜና

በአዲስ አበባ 18 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ መሞታቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ 18 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ መሞታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥ 1ሺህ 500 ሰዎች በውሾች ተነክሰዋል ተብሏል ራቢስ በተሰኘ ቫይረስ አማካኝነት በሚከሰተው የእብድ ውሻ በሽታ የተነሳ ባለፋት ስምንት ወራት በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ የ18 ሰዎች ህይወት ማለፋን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። በኢንስቲትዩቱ የእንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዲቪዥን ክፍል ተመራማሪ አቶ መስፍን አክሊሉ እንደተናገሩት እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከተሞች የውሾች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል። በተለይም ደግሞ ባለቤት አልባ ውሾችን በማስወገድ በኩል በቂ ስራ ባለመሰራቱ ሁኔታውን እንዲባባስ አድርጓል።ባለፋት ስምንት ወራት በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ 1462 ሰዎች የውሻ ንክሻ እንዳጋጠማቸውና ክትባት እንደወሰዱ የተናገሩት  ተመራማሪው በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ይህን በሽታ ለመግታት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በጋራ መስራት…
Read More
ኢሠማኮ መንግስት ለአደጋ ጊዜ በሚል ከተቀጣሪ ሰራተኞች ገንዘብ ለመሰብሰብ ማቀዱን ተቃወመ

ኢሠማኮ መንግስት ለአደጋ ጊዜ በሚል ከተቀጣሪ ሰራተኞች ገንዘብ ለመሰብሰብ ማቀዱን ተቃወመ

የመንግስት እና የግል ተቋማት ከሚሰጧቸው የተለያዩ አገልግሎቶች “ለአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” የሚሆን ገቢ እንዲሰበስቡ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ባሳለፍነው ሳምንት ለፓርላማ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሠማኮ) መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሳይወስን ገንዘብ ለመሰብሰብ አዲስ ረቂቅ ማስተዋወቁ ማንም አይጠይቀኝም ከሚል የመነጨ ነው ብሏል፡፡ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን በፓርላማ የፀደቀውን አዋጅ ሳያስተገብር ከሰራተኛው ላይ ገንዘብ ለመሰብሰብ አዲስ ረቂቅ ማስተዋወቁ ማንም አይጠይቀኝም ከሚል የመነጨ ነውም ብሏል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን እንደ አዲስ እንዲቋቋም የታሰበው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ለተቀጣሪ ሰራተኞች ራሱን የቻለ አደጋ ነው ብሎታል። ከሳምንት በፊት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጁ የቀረበው የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋትና ስራ…
Read More
የብሪታንያው ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

የብሪታንያው ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

ኢትዮዽያ የእንግሊዙን ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ ተገልጿል። ዋና መስሪያ ቤቱን በእንግሊዝ ያደረገው ግሪን ሞሽን የመኪና ኪራይ አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮጵያን  80ኛ መዳረሻው በማድረግ ስራ መጀመሩ ተሰምቷል። ግሪን ሞሽን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ያደረገው በመኪና ኪራይ ዘርፍ ላለፉት 10 ዓመታት ሲሰራ የቆየው ኤክሰለንት የመኪና ኪራይ ድርጅት ነው፡፡ ስራውን በአዲስ አበባ እውን ለማድረግ ሁለት ዓመት የፈጀ ድርድር ሲደረግ ቆይቷል ተብሏል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ለስብሰባ ለመሳሰሉት ጉዳዮች አዲስ አበባን የሚረግጡ ተጓዦች በቆይታቸው የመኪና ኪራይ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ገና ከመምጣታቸው አስቀድሞ የመኪና አይነቱንም ክፍያውንም መፈፀም እንደሚችሉ ተናግሯል። ይህ በመሆኑም የሀገርን ገፅታ ከፍ ያደርጋል የውጭ ምንዛሪ ግኝትንም ለመፍጠር እድል…
Read More
ኤርትራዊያንን በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መኪና ሲያጓጉዙ የተገኙ ወታደሮች በእስራት ተቀጡ

ኤርትራዊያንን በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መኪና ሲያጓጉዙ የተገኙ ወታደሮች በእስራት ተቀጡ

በሰዎች ዝውውር የተከሰሱ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በእሥራት ተቀጥተዋል። በህገ ወጥ የሠዎች ዝውውር ተሠማርተዋል የተባሉ አንድ ከፍተኛ የአገር መከላከያ ሠራዊት አዛዥን ጨምሮ ሁለት የሠራዊቱ አባላት በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት ተቀጥተዋል፡፡ አባላቱ ቅጣቱ የተላለፈባቸው ትናንት በአርባምንጭ ከተማ በተሰየመው የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባሳለፈው የፍርድ ውሳኔ ነው  ተብሏል፡፡ ቅጣቱ የተወሰነው በሠራዊቱ የደቡብ ዕዝ 202ኛ ኮር 1ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል መብራቱ ታዴ እና በሬጅመንቱ የኦራል አሽከርካሪ በሆነው ወታደር ጌታቸው ክብረት በተባሉት  ላይ እንደሆነ ዶቸቪሌ ዘግቧል። አዛዡ እና የሰራዊቱ አባል ቅጣቱ የተወሰነባቸው ህዳር 16 2016 ዓ.ም 52 ኤርትራዊያንን በሠራዊቱ የኦራል ተሽከርካሪ በመጫን ወደ ኬኒያ በማሻገር ላይ እንዳሉ በመያዛቸው መሆኑን የጋሞ ዞን ከፍተኛ…
Read More
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወጋገን ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኙ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወጋገን ባንክ የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኙ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወጋገን ባንክ በኢትዮጵያ የመጀመርያው የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኙ። ሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ኢንቨስትመንት ባንክ እና ወጋገን ካፒታል አክሲዮን ማህበር ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ያገኙት የመጀመርያው የኢንቨስትመንት ባንኮች ሆነዋል። እነዚህ ባንኮች ራሳቸውን ችለው የተቋቋሙ የካፒታል ገበያ ስራ ብቻ የሚሰሩ የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው የተባለ ሲሆን በተጨማሪም ለአምስት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ፈቃድ ተሰጥቷል። ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች መካከልም ኢትዮ-ፊደሊቲ ሴኩሪቲስ አ.ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ (Securities Dealer) ፣ ኤች ኤስ ቲ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ. ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ፣ ኢኩዥን የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ኃ.የተ.የግ. ማ - የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ መሆናቸው ተጠቁሟል። ፈቃድ የተሰጣቸው አገልግሎት ሰጪዎች…
Read More
ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቃል ተባለ

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቃል ተባለ

ከ15 ዓመት በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ በያዝነው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ውቅት እንዳሉት ህዳሴ ግድብን ከ6 ወር በኋላ እንመርቃለን ብለዋል፡፡ መንግስት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ መንግስት ጋር በተለይም ከደህንነት መስሪያ ቤት ጋር ህዳሴን በተመለከተ ውይይት አድርገናል የተለያዩ ሃሳቦችም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቅርበናል ብለዋል፡፡ መንግስት በህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ዝግጁ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል:: የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ 15 ዓመታት ሊሞሉት አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል።…
Read More
ጤናማና ዘላቂ የአመጋገብ ሥርዓትን ለማበጀት ያቀደ ”ኢኮ ፉድ ሲስተም” የተሰኘ ፕሮግራም ይፋ ተደረገ

ጤናማና ዘላቂ የአመጋገብ ሥርዓትን ለማበጀት ያቀደ ”ኢኮ ፉድ ሲስተም” የተሰኘ ፕሮግራም ይፋ ተደረገ

ፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ያለውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዲሁም ሰዎችን ላላስፈላጊ ውፍረት የሚዳርገውን ከመጠን በላይ የሆነ የአመጋገብ ሥርዓትን የሚያጠና ነው ተብሎለታል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎችን እና የተለያዩ ችግሮችን መቋቋም የሚችሉ የምግብ ስርዓትን ለማቅረብ ያለመ መሆኑ የተነገረለት ይህ ፕሮግራም የአዲስ አበባ ነዋሪን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል። ፕሮግራሙ በከተሞች ላይ ያለው የስርዓተ ምግብ ምን ሁኔታ ላይ ነው፣ ምንስ መስተካከል አለበት የሚሉ እና ሌሎች ጥናቶችም እየከወነ ለፖሊሲ አውጭዎች እና ለሚመለከታቸው ተቋማት መረጃ የመስጠት ስራ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይሰራል ተብሏል። በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የስነ ምግብ እና የአካባቢ ጤና ዳይሬክተር ዶክተር ማስረሻ ተሰማ እንዳሉት ፕሮጀክቱ በከተማዎች ላይ ያለን የስርአተ ምግብ ሁኔታን እየተከታተሉ መረጃ…
Read More
መንግሥት በአማራ ክልል የተናጥል የተኩስ አቁም እንዲያውጅ ተጠየቀ

መንግሥት በአማራ ክልል የተናጥል የተኩስ አቁም እንዲያውጅ ተጠየቀ

እስረኞች እንዲፈቱና በክልሉ ያለው ግጭት እንዲቆምም ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል በሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር) የተመራ የኮሚሽኑ ልዑክ ወደ አማራ ክልል ባህርዳር ከተማ አቅንቶ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል። የኮሚሽኑ ልዑክ ወደ አማራ ክልል ያቀናው የአማራ ክልል የአጃንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በሚካሄድበት አስቻይ ሁኔታ ላይ ከክልሉ መንግስት ጋር ለመነጋገር ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በተገኙበት በዚህ ውይይት የኮሚሽኑ የእስካሁን ስራዎች በዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ(ፕሮፌሰር) ቀርቦ የክልሉ አመራሮች ስለ ኮሚሽኑ የስራ እንቅስቃሴ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል። ከኮሚሽኑ የቅርብ ጊዜ የስራ እቅዶች መካከል አንዱ በአማራ ክልል የአጀንዳ ልየታ የምክክር ምዕራፍ ማካሄድ ስለመሆኑ የኮሚሽኑ…
Read More
የአፍሪካ ወጣቶች ሮቦቲክስ ውድድር በአዲስ አበባ ተጀመረ

የአፍሪካ ወጣቶች ሮቦቲክስ ውድድር በአዲስ አበባ ተጀመረ

የአፍሪካ ወጣቶች የሮቦቲክስ ፈጠራ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት 3ኛው የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር ዛሬ በታላቅ ድምቀት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተጀምሯል። የኢትዮ ሮቦቲክስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰናይክረም መኮንን ለሦስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ የመጀመሪያ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ፣ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፈጠራ ችሎታቸው ይወዳደራሉ፤ ውድድሩም በዲዛይን፣ በኢንጂነሪንግ እና በአውቶኖሚ ኮዲንግ ላይ እንደሚያተኩር በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ላይ አስረድተዋል። አቶ ሰናይክረም የውድድሩ ዓላማ ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት ማዳበርና ማበረታታት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በዚህ ውድድር አሸናፊ የሚሆኑ ተማሪዎች የዋንጫ ሽልማት እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተፈረመ የምስክር ወረቀት እንደሚያገኙ አስታውቀዋል። ለፍጻሜ የሚበቁ ተማሪዎች አገራቸውን ወክለው በአሜሪካ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ…
Read More
አሜሪካንን ጨምሮ ከ25 በላይ ሀገራት በትግራይ ያለው አለመረጋጋት አሳስቦናል አሉ

አሜሪካንን ጨምሮ ከ25 በላይ ሀገራት በትግራይ ያለው አለመረጋጋት አሳስቦናል አሉ

በትግራይ ክልል በጊዜያዊ አስተዳድሩ እና በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ቡድን መካከል ግጭት መከሰቱን ተከትሎ የመፈንቅለ መንግስት እየተፈጸመ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳድር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ በመቀሌ እና አዲ አበባ በሰጧቸው መግለጫዎች ላይ እንዳሉት የህወሃት አንዱ ክንፍ በጊዜያዊ አስተዳድሩ ላይ አመራሮችን መሾም፣ ማህተም መቀማት፣ ቢሮዎችን መቆጣጠር እና ሌሎች ህጋዊ ያልሆኑ ስራዎችን እያካሄደ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በትግራይ ክልል አለመረጋጋት የተፈጠረ ሲሆን በክልሉ ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚሉ ስጋቶች አይለዋል፡፡ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ከ20 በላይ ሀገራትም በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡ የጋራ መግለጫውን ካወጡ ሀገራት መካከል አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ጀርመን፣ፈረንሳይ፣ ስዊድን፣ ቤልጂየም እና…
Read More