20
Mar
ከ15 ዓመት በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ በያዝነው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ውቅት እንዳሉት ህዳሴ ግድብን ከ6 ወር በኋላ እንመርቃለን ብለዋል፡፡ መንግስት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ መንግስት ጋር በተለይም ከደህንነት መስሪያ ቤት ጋር ህዳሴን በተመለከተ ውይይት አድርገናል የተለያዩ ሃሳቦችም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቅርበናል ብለዋል፡፡ መንግስት በህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ዝግጁ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል:: የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ 15 ዓመታት ሊሞሉት አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል።…