ዜና

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትን እገዛ ጠየቀ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስትን እገዛ ጠየቀ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው የፌደራል መንግስትን እገዛ የጠየቀው። ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው “ከጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አንዳንድ የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ከተልኮ ወጭ የአንድ ጠባብ ቡድን የስልጣን ጥም ለማርካት በማለት ግልፅ የመፈንቅለ መንግስት እንስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል” ብሏል። “በዚህ ሳምንትም በተመሳሳይ በሰሜን ምስራቅና በደቡብ ግንባር አዛዦች እንቅስቃሴው በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል” ብሏል መግለጫው። ይህንን አደገኛ እንቅስቃሴ ለመግታት እና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ሁሉ ለማስቆም የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ለትግራይ ጦር ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ትእዛዝ ቢሰጥም ማስቆም እንዳልቻለ አስታውቋል። ሁኔታው እልባት ባለማግኘቱ የግንባሩ የጦር አዛዦች  እገዳ እንደተጣለባቸው ያመላከተው መግለጫው፤ የጸጥታ ቢሮ…
Read More
የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብር በጫና እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግሩ

የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብር በጫና እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተናግሩ

የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብርና ታክስ በተጨማሪ በሌሎች ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ ተገለፀ የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ፎረም በከተማው ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ከባድ ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን ገልጿል። ፎረሙ የባለሀብቶችን ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል። የባለአብቶች ፕሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ለካፒታል እንደገለጹት፣ ባለሀብቶቹ ያላግባብ ድርጅቶቻቸው መታሸግ፣ መፍረስ፣ መነጠቅ (መቀማት)፣ ሥራ እንዲያቆሙ መደረግ፣ ያላመኑበትን ከፍተኛ ግብርና ታክስ ለማስከፈል ማስገደድ፣ የባንክ አካውንታቸው መታገድ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ወይም እንዳይገቡ እየተደረጉ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ በስልክ ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረስ፣ የማያምኑበትን አሰልቺና ተደጋጋሚ መዋጮዎች መጠየቅ፣ እንዲሁም ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳይከውኑ ማዋከብ፣ የብድር አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ያለማግኘት እና የመሳሰሉት ችግሮች እየደረሱባቸው መሆኑን ሰምተናል ብለዋል። ይህን ተከትሎ ፎረሙ…
Read More
ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን ሳተላይት በ2026 ልታመጥቅ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን ሳተላይት በ2026 ልታመጥቅ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂስፓሻል ኢኒስቲትዩት እንደገለጸው በፈረንጆቹ 2026 ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማምጠቅ በሥራ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ ታመጥቃታለች የተባለው ሶስተኛ ሳተላይት ከዚህ ቀደም መጥቀው አገልግሎት ጊዜያቸው ካበቁት ሁለት ሳታላይቶች የተሻለ የምስል ጥራት ይኖራታል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማምጠቅ ከቻይና መንግስት ጋር ተፈራርማ እየሰራች መሆኑን የነገሩን በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት የሳተላይት ክትትል ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ፉፋ ናቸው፡፡ አቶ ተስፋዬ ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን እና የተሻለ የመሬት ምልከታ ጥራት ያላትን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማምጠቅ ስራ መጀመሯን አስረድተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማልማት በምን ያክል ገንዘብ ከቻይና ጋር…
Read More
ኢትዮጵያ ስድስት የጭነት መርከቦችን ልትገዛ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ስድስት የጭነት መርከቦችን ልትገዛ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስድስት አዳዲስ የጭነት መርከቦችን ግዢ ሊፈፀም እንደሆነ አስታውቋል። 62 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሁለት አልትራማክስ የደረቅ ብትን ጭነት መርከቦች በአጭር ግዜ ተገዝተው አገልግሎት እንደሚጀምሩ ድርጅቱ ገልጿል፡፡ የቀሪ አራት መርከቦች ግዥ በቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ መርከቦቹን የምትገዛው የሀገሪቱን የገቢ ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ያግዛሉ በሚል ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ላይ 10 መርከቦች እንዳሏት ይነገራል። ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ መረከቧ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቅርቡ ባህር ዳር እና ሀዋሳ የተሰኙ ሁለት መርከቦች ለኪሳራ ዳርገውኛል በሚል መሸጡ ይታወሳል። በተሸጡት ሁለት መርከቦች…
Read More
የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

ከ3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገለፀ፡፡ የግብር ዕዳ ያለባቸውና በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ዕዳቸውን ለመክፈል ፈቃደኛ ያልሆኑ 62 ግለሰቦችን ላይ ነው ትዕዛዙ የተላለፈው:: በዚህም ቢሮው በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀፅ ከ1-3 ለተቋሙ በተሰጠ ስልጣን መሰረት ከሀገር እንዳይወጡ ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዝርዝራቸውን ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡ ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የግብር ዕዳቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚሰወሩ ግብር ከፋዮችን በመከታተል ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የዕዳ ክትትልና አስተዳደር የስራ ክፍልን በአዲስ መልክ በማደራጀት ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል:: በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ከ6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ…
Read More
በኢትዮጵያ የኮንዶም እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የኮንዶም እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ

በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የኮንዶም እጥረት ለመቅረፍ የግል የመድሃኒት አስመጪዎች ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ጥሪ እየቀረበ ነው፡፡ በየዓመቱ በመንግስትና በግብረሰናይ ድርጅቶች ከ90 ሚሊዮን ያልዘለለ አቅርቦት ቢኖርም ዓመታዊ ፍላጎቱ ግን 270 ሚሊዮን ይደርሳል፤ ቀድሞውንም ቢሆን እጅግ የተራራቀ አቅርቦትና ፍላጎት ያለበት ኮንዶም አሁን ደግሞ የአሜሪካ መንግስት የተራድኦ ድርጅት የሆነው ዩኤስ አይዲ የሚሰጠውን ድጋፍ ማገዱ እጥረቱን አባብሶታል፡፡ ከዚህ ቀደም በነፃ ይታደል የነበረው፣አልፎ አልፎም በጣም በዝቅተኛ ዋጋ በየሱቁ ይገኝ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን የአንድ ኮንዶም አማካኝ ዋጋው 50 ብር ደርሷል፡፡ እንደ ጋምቤላ ባሉ የክልል ከተሞች እጥረቱን ተከትሎ በተፈጠረ የዋጋ ንረት አንድ ኮንዶም እስከ 250 ብር እተሸጠ መሆኑን ተነግሯል፡፡ በዚህና በሌላውም ምክንያት ኮንዶምን የመጠቀም ዝንባሌ መቀነስ…
Read More
ኢትዮጵያ 5000 ዘመናዊ ሩሲያ ሰራሽ ተሽከርካሪዎችን ልታስግባ ነው

ኢትዮጵያ 5000 ዘመናዊ ሩሲያ ሰራሽ ተሽከርካሪዎችን ልታስግባ ነው

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገሩት፤ ተሽከርካሪዎቹ ከሀገሪቱ መልክዓ ምድር ጋር አብረው የሚሄዱ እና የዩሮ 5 የሞተር የተገጠመላቸው በመሆኑ የአየር ብክለት ተፅእኗቸው አነስተኛ ነው። በኢትዮጵያ ያሉ አብዛኛዎቹ ተሽከርካሪዎች ዩሮ 2 እና ዩሮ 3 የሞተር ብቃት ያላቸው ሲሆኑ፤ ሩሲያ ሰራሾቹ ካማዝ ተሽከርካሪዎች ግን በዚህ ረገድ አዲስ ምዕራፍን የገለጡ ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ የንግድ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እንዳገዛቸውም ነው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንቱ የተናገሩት። ተሽከርካሪዎቹን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባው የባዝራ ሞተር ድርጅት ማናጀር ያይራድ አስናቀ በበኩላቸው፤ ተሽከርካሪዎቹ በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ ወር ወደ ኢትዮጵያ መግባት ይጀምራሉ ብለዋል። በቀጣይ የሕዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችንም ጭምር ለማስገባት እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነም…
Read More
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር ወለድ መጠኖች ላይ ጭማሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከየካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ በተለያዩ የብድር ዓይነቶች ላይ ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል። ይህ ጭማሪ የመጣው መንግስት የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት አካል እንደሆነ ባንኩ ገልጿል። በተደረገው ማስተካከያ መሰረት፣ የግብርና ብድሮች እስከ 15.5%፣ የንግድ ብድሮች እስከ 18%፣ የወጪ ንግድ ብድሮች እስከ 14%፣ የግል ብድሮች ደግሞ እስከ 15% ጭማሪ አሳይተዋል። ይሁንና ባንኩ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድሮች የወለድ ምጣኔው በነበረበት በ12 በመቶ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል ብድሮች በስምምነቱ ውል ላይ በመመስረት ከ11 በመቶ እስከ 13 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ ለየት ያለ ከፍተኛ ዋጋ ላላቸው ደንበኞች ሰራተኞች የግል ብድሮች…
Read More
የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከ3 ሺህ በላይ ሠራተኞቹን አሰናበተ

የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከ3 ሺህ በላይ ሠራተኞቹን አሰናበተ

በአፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው ከሰም የስኳር ፋብሪካ፣ በክልሉ እየተከሰተ ባለው ለወራት የቀጠለ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ይፋ ባደረገ በወሩ፣ ከ3,700 በላይ ሠራተኞቹን ከሥራ ማሰናበቱ ታወቀ። በክልሉ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመጣው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በካምፕ የተጠለሉ 3,750 ቋሚና ጊዜያዊ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች፣ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባልጠበቁት ሁኔታ ከሥራ ተሰናብተዋል። ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ 123 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ከሰም ስኳር ፋብሪካ ከ10 ዓመት በፊት ነበር ስኳር ማምረት የጀመረው፡፡ በዓመት 260 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም የነበረው ይህ ስኳር ፋብሪካ በአዋሽ አካባቢ ባጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ስራ አቁሟል፡፡ በ20 ሺህ ሄክታር መሬት…
Read More
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በኤርትራ ጉዳይ የሰጡት ሀሳብ የግላቸው እንጂ የመንግስት አቋም አይደለም ተባለ

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በኤርትራ ጉዳይ የሰጡት ሀሳብ የግላቸው እንጂ የመንግስት አቋም አይደለም ተባለ

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በኤርትራ ጉዳይ የሰጡት ሀሳብ የመንግስት አቋም አለመሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫው ላይ ከጋዜጠኞች ከቀረበላቸው ጥያቄዎች መካከል የቀድሞው የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ሙላቱ (ዶ/ር) ኤርትራን አስመልክቶ ያጋሩት ጽሁፍ ነው። የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከሁለት ሳምንትት በፊት አልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ "የኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ በምስራቅ አፍሪካ አዲስ ግጭት እንዳይከፈት ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው" ማለታቸው ይታወሳል። የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የተነሱትን ነጥቦች አጣጥለዋል። ስለ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጽሁፍ ኤርትራ ምላሽ የተጠየቁት አምባሳደር…
Read More