ETRSS-2

ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን ሳተላይት በ2026 ልታመጥቅ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን ሳተላይት በ2026 ልታመጥቅ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂስፓሻል ኢኒስቲትዩት እንደገለጸው በፈረንጆቹ 2026 ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማምጠቅ በሥራ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ ቀጣይ ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ ታመጥቃታለች የተባለው ሶስተኛ ሳተላይት ከዚህ ቀደም መጥቀው አገልግሎት ጊዜያቸው ካበቁት ሁለት ሳታላይቶች የተሻለ የምስል ጥራት ይኖራታል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማምጠቅ ከቻይና መንግስት ጋር ተፈራርማ እየሰራች መሆኑን የነገሩን በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት የሳተላይት ክትትል ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ፉፋ ናቸው፡፡ አቶ ተስፋዬ ኢትዮጵያ ሶስተኛዋን እና የተሻለ የመሬት ምልከታ ጥራት ያላትን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማምጠቅ ስራ መጀመሯን አስረድተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ሶስተኛዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ለማልማት በምን ያክል ገንዘብ ከቻይና ጋር…
Read More