ዜና

የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት ተባረሩ

የእስራኤል አምባሳደር ከአፍሪካ ህብረት ተባረሩ

የእስራኤል አምባሳደር ከሩዋንዳ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ላይ በአፍሪካ ህብረት ተባረሩ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት አብርሃም ንጉሴ፣ ዛሬ መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓ.ም. በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተካሄደው 31ኛዉ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት እንዲወጡ ተደርጓል። ይህ የሆነው በርካታ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሩ በዚሁ የሐዘን ስነ-ስርዓት ላይ መገኘታቸውን በመቃወማቸው መሆኑ ተዘግቧል ። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦረን ማርሞርስቴይን ድርጊቱን "አሳፋሪ" እና "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ በጽኑ አውግዘዋል። "በአዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል አምባሳደር በተጋበዙበት፣ በሩዋንዳ የቱትሲ የዘር ማጥፋት ሰለባዎችን ለማስታወስ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ፀረ-እስራኤላዊ የፖለቲካ አመለካከቶችን ማስተዋወቃቸው እጅግ አሳፋሪ ነው" ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ማርሞርስቴይን…
Read More
ኢትዮጵያ በውጭ ባንኮች ላይ የአምስት ቢሊዮን ብር ግዴታ ጣለች

ኢትዮጵያ በውጭ ባንኮች ላይ የአምስት ቢሊዮን ብር ግዴታ ጣለች

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ባንኮች አምስት ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ሟሟላት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው አዲስ መመሪያ ጥብቅ ቅደመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠ ነው ተብሏል። መመሪያው በባንኩ ዘርፍ የውጭ ሀገራት ተሳትፎን የውጭ ባንክ ተቀጥላ፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ እና የእንደራሴ ቢሮ ብሎ የሚከፍል ሲሆን ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት የወንጀል እና የታክስ ማጣራትን ጨምሮ ጥብቅ ምርምራዎችን ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው አስቀምጧል። የውጭ ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ ለማስቀመጥ እና ለመጠቀም ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን ክፍያን በተመለከተ ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ለምርመራ 200 ሺህ፣ ለፈቃድ 400 ሺህ እና ለእድሳት 400 ሺህ ብር መክፈል እንዳለባቸው ተቀምጧል። መመሪያው የሀገር ውስጥ ባንኮች ካፒታላቸውን መጨመር፣ የመረጃ አጠቃቀም ሕጋቸውን ከሀገሪቱ…
Read More
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ32 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ32 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ለስድሰት የልማት ፕሮጀክቶች የሚውል የ32 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ለስድሰት ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል የ240 ሚሊየን ዩሮ ወይም የ32.3 ቢሊየን ብር የልማት ድጋፍ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን አስተዳደርና አካታችነትን በማሻሻል መረጋጋትን ማስፈን የሚለው ይገኝበታል። በተጨማሪም በግጭት የተጉዱ የጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስና እንዲሁም ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ የግብርና ስራዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በመጠቀም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ልማትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማምጣት፣ የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር ደግሞ ሌሎቹ የድጋፍ ስምምነቱ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸው ተጠቁሟል። በፊርማ ስነ…
Read More
ኢትዮጵያ ለቤት ሰራተኞች የጡረታ ክፍያ ልትጀምር ነው

ኢትዮጵያ ለቤት ሰራተኞች የጡረታ ክፍያ ልትጀምር ነው

የቤት ሠራተኞችን የጡረታ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ ደንብ በ6 ወር ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ የቤት ሠራተኞች ጡረታን ጨምሮ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች ደንብ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድነት የኢትዮጵያ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ማህበራት ሕብረት አስታውቋል። የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ሂሩት አበራ የቤት ሠራተኞችን ሕግ በሚመለከት በዓለም አቀፉ ኮንቬንሽን 189 በተቀመጠው ሕግ መሠረት በቀጥታ ለመተግበር አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ፤ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ ደንቡና የሥራ ቅጥር ውሉ እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል፡፡ ይኸው ደንብ በረቂቅ ደረጃ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል። ለአብነትም በቋሚነት የሚሰሩ ሠራተኞች በሥራ ቦታቸው ላይ የመኖር፣ ተመላላሽ…
Read More
ኢትዮጵያ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ብሔራዊ ግዳጅ ልትጥል ነው

ኢትዮጵያ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ብሔራዊ ግዳጅ ልትጥል ነው

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታውቋል። ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ  ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል። ላለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል። ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣለች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣለች

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ እንዲጣል ያዘዙ ሲሆን ኢትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ተጥሎባታል። ፕሬዚዳንቱ በነጩ ቤተ መንግሥት በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል። እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ እርምጃው አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል። ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከተሞች አበባ፣ ቡና፣ የቆዳ እና አልባሳት ምርቶችን በመላክ ላይ ስትሆን ተጨማሪ 10 በመቶ ቀረጥ ለመክፈል ትገደዳለች። አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት…
Read More
የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ባንኮች የምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን ህግ ተቃወመ

የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር ባንኮች የምሽት አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደውን ህግ ተቃወመ

ባንኮች እስከ ምሽት 3፡30 ሰዓት ድረስ ክፍት እንዲሆኑ የሚያስገድደዉ ደንብ ከባንኮች አሰራር ጋር የማይጣጣም ነዉ ሲል የባንኮች ማህበር አስታወቀ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣው ባንኮች እስከ ምሽት 3:30 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ከባንኮች አሠራር ጋር የማይጣጣም መሆኑን ማህበሩ ገልጿል፡፡ ባንኮች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አማካይነት የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶችን ለደንበኞቻቸው በቀላሉ ማቅረብ እየቻሉ በመሆኑ፣ የምሽት አገልግሎት አላስፈላጊና አግባብነት የሌለው መሆኑን የባንኮች ማህበር አስታዉቋል። የባንኮች ማህበር ዋና ጸሀፊ አቶ ደምሰው ሞገስ እንደሚገልጹት፣ደንበኞች በፖስ ወይም ኤቴኤም ማሽኖች፣ በተንቀሳቃሽ ስልክ የባንክ መተግበሪያዎችና በኢንተርኔት ባንኪንግ አማካይነት የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት ስለሚችሉ ባንኮች እስከ ምሽት ክፍት ሆነው መቆየት አለባቸዉ የሚለዉ አስገዳጅ መመሪያ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡ በተጨማሪም…
Read More
ኢትዮጵያ ለሙዚቀኞች የሮያሊቲ ክፍያ መክፈል ልትጀምር ነው

ኢትዮጵያ ለሙዚቀኞች የሮያሊቲ ክፍያ መክፈል ልትጀምር ነው

የሮያሊቲ ክፍያ ከመጪው ሐምሌ ወር ጀምሮ መክፈል ይጀመራል ተብሏል የሙዚቀኞች የሮያለቲ ክፍያ ከሀምሌ ወር ጀምሮ መክፈል እንደሚጀመር ተገልጿል። መገናኛ ብዙሀን ለሙዚቀኞች የሮያሊቲ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስገደደው መመሪያ የፊታችን ሀምሌ 1ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። የሮያሊቲ ክፍያ ረቂቅ መመሪያው የሚመለከታቸው አካላትን ባሳተፈ መንገድ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን  ህጉን ለማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ቢበዛ ከአምስት ወር በኃላ ፀድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል ተናግረዋል። በኢትዮጲያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አማካኝነት የተሰናደው ይህ ውይይት፣ሙዚቀኞች፣ ፕሮዲውሰሮች፣ደራሲያን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል። ውይይቱ በዋናነት በሙዚቀኞች ሮያሊቲ ክፍያ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የክፍያ ቀመር  ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ…
Read More
አደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18.6 ቢሊየን ብር ተመደበ

አደይ አበባ ስታዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18.6 ቢሊየን ብር ተመደበ

ኢትዮጵያ የብሔራዊ ስታድየሟን ግንባታ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዷ ተገለጸ 62 ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው ከተጀመረ 10 ዓመት አልፎታል በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘውን አደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ 18 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገልጿል፡፡ አሁን የአደይ አበባ ስቴዲየም ቀሪ ስራዎችን ከሁለት አመት ባነሰ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ተብሏል። የስታዲየሙን የማጠናቀቂያ ሥራዎች ለማከናወን 18 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ውል መገባቱን የባህልና ስፖርት ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በሁሉም ክልሎች አንድ ስታዲየም ያላት ቢህንም ከዚህ ውስጥ አንዱም የካፍን ደረጃ የማያሟላ ሲሆን በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለው እና 62 ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው አደይ አበባ ስታዲየም ግንባታው በተለያዩ ምክንያቶች መጠናቀቅ…
Read More
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ50 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ እንደሚያወጣ ገለጸ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ50 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ እንደሚያወጣ ገለጸ

ብሔራዊ ባንክ የዶላር ጨረታ በየ15 ቀኑ በተከታታይ አወጣለሁም ብሏል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንት መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ እንደሚጀምር አስታወቀ። ጨረታዎቹ ለሚቀጥሉት በርካታ ወራት የሚካሄዱ ሲሆን፣ ዓላማውም የማዕከላዊ ባንኩን የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት ግብን ለማሳካት ነው ብሏል። የማዕከላዊ ባንኩ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በታሪኩ ከፍተኛው እንደሆነ ገልጾ በተለይ ከቅርብ ወራት ወዲህ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ብቸኛው የወርቅ ገዥ ለሆነው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቀረበው የወርቅ መጠን ከፍተኛ መሆን የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት ከተገመተው በላይ እንዲጨምር እንዳደረገው ጠቁሟል። ከዚህ ከተጠበቀው በላይ ከሆነው የውጭ ምንዛሪ ግኝት አንጻር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቀጣይ ወራት በመደበኛነት በየሁለት ሳምንቱ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታዎችን ለማካሄድ መወሰኑን አሳውቋል።…
Read More