23
Jun
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዳጅ ለገበያ እንደምታቀርብ መናገራቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ካሉ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ከመስከረም ወር ጀምሮ ነዳጇን ለገበያ ማቅረብ እንደምትጀምር ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰባት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ነዳጅ ማውጣት ጀመረች በሚል ለኢትዮጵያዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡ ይሁንና ይህ ከሆነ ከሰባት ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ነዳጅ ለገበያ እንደምታቀርብ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በሶማሊ ክልል ኦጋዴን አካባቢ ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ እንዳላት በተደጋጋሚ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን የቻይና ፖሊሲጂኤል ኩባንያ ነዳጅ ለማውጣት በሂደት ላይ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የነዳጅ ፍላጎቷን ሙሉ ለሙሉ…