ዜና

አሜሪካ ፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም እቅዳቸውን እንዲያሳውቁ ጠየቀች

አሜሪካ ፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሰላም እቅዳቸውን እንዲያሳውቁ ጠየቀች

አሜሪካ ዛሬ አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ በኩል ለፌዴራል መንግሥት እና ለታጣቂዎች መልዕክት አስተላልፋለች። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት በመላው ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለጉዳት የዳረጉ ግጭቶች ሰላማዊና ትክክለኛ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። አምባሳደሩ፥ ለታጣቂ ኃይሎች እና ለፌደራል መንግስት ባስተላለፉት መልዕክት ህዝብን እንዲያስቀድሙ ጥሪ አቅርበዋል። " ጦርነቱን ማቆም፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ መርዳት እና ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ እና የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል። " በትጥቅ ትግል ስም የሚፈጸሙ ህገወጥ እና የኃይል እርምጃዎች ሊቆሙ ይገባል " ብለዋል። አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በመልዕክታቸው ለፋኖ ፣ ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (OLA) እና ለፌደራል መንግስት የተናጠል መልዕክት…
Read More
መንግሥት ሐኪሞች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ኢሰመኮ አሳሰበ

መንግሥት ሐኪሞች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ኢሰመኮ አሳሰበ

በሕክምና ተቋማት በመካሄድ ላይ ያሉ የሥራ ማቆም አድማዎች ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች በር እንዳይከፍቱ ትኩረት እንዲሰጣቸውም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሕክምና ባለሙያዎች በሕክምና ተቋማት ውስጥ በማድረግ ላይ የሚገኙት የሥራ ማቆም አድማ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ በመንግሥት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳያስከትሉ ትኩረት ሊሰጣቸው እና አፋጣኝ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚገባ ያሳስባል። ኢሰመኮ አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ከሥራ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን መንግሥት እንዲመልስ ሰጥተናል ያሉት የ30 ቀናት የጊዜ ገደብ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁን ተከትሎ በመንግሥት እና በሕክምና ባለሙያዎች በመወሰድ ላይ የሚገኙትን እርምጃዎች በመከታተል ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት ኢሰመኮ…
Read More
የገቢዎች ሚንስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ649 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

የገቢዎች ሚንስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ649 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

ሚኒስቴሩ በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 649 ቢሊዮን ብር ሰብስቤያለሁ ብሏል ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ 74 በመቶ ወይም የ279 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡ ከተሰበሰበው ገቢ 345.9 ቢሊየን ብሩ ከታክስ የተገኘ ሲሆን ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 307.2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገልጿል። ገቢው በመቶ ቢሊዮኖች ከአምናው ከፍ ያለበት ምክንያት ግን በሪፖርቱ አልተብራራም፡፡ በሌላ በኩል ህገ-ወጥ ንግድ ፣ ገቢን መደበቅ ፣ ግብይትን ያለ ደረሰኝ መከወን ፣ ግብር ስወራና ታክስ ማጭበርበር አሁንም ፈተና ሆነውብኛል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡ ተሰውሮብኝ ነበር ያለውን ገቢ ለማግኘትም በድንገተኛ ፍተሻ ፣ በሒሳብ ምርመራ ወይም ኦዲትና መሰል ስራዎች የህግ ማስከበር ስራ ሰርቻለሁ ብሏል፡፡ በዚህም 7 ሺህ 583 የሒሳብ…
Read More
በካቻ የነዳጅ ክፍያ መክፈል ተጀመረ

በካቻ የነዳጅ ክፍያ መክፈል ተጀመረ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ክፍያ ሰነድ አውጪ የሆነው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አሽከርካሪዎች ካቻን በመጠቀም በቀላሉ የነዳጅ ክፍያን የሚከፍሉበትን አገልግሎት በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል። አገልግሎቱም ደንበኞች የካቻን መተግበሪያ በመጠቀም ፣ በ“Push USSD Notification” እንዲሁም በQR ኮድ ስካን በማድረግ በቀላሉ የነዳጅ ክፍያን መፈፀም የሚያስችል ሲሆን የካቻ ደንበኛ ያልሆነ ማንኛውምአሽከርካሪ መተግበሪያውን ከፕሌይስቶር ወይም አፕስቶር በማውረድ ከማንኛውም ባንክ ወደ ካቻ ገንዘብ በማስተላለፍ  ወዲያውኑ ክፍያ መፈፀም እንደሚያስችል ተገልጿል። "የዛሬው ምርቃት ካቻ ለማህበረሰባችን ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ፉይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ለሚያደርገው ጉዞ አንድ እርምጃ የሚያግዘን ነው"ያሉት የካቻ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሀም ጥላሁን "በቀጣይም ካቻ በአሽከርካሪዎች ላይ ያለውን የፋይናንስ ጫና…
Read More
ኢትዮጵያ የአልኮል መጠጦችን በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይሰራጩ የሚከለክል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የአልኮል መጠጦችን በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይሰራጩ የሚከለክል ረቂቅ ህግ አዘጋጀች

የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ ተዘጋጅቷል የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሰልጣን የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ አዘጋጅቶ በሒደት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የአልኮል ምርቶችን እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ በህግ ማገዷ ይታወቃል። የአልኮል አምራች ተቋማት በአሁን ሰዓት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም፤ ምርታቸውን እያስተዋቁ እና ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች እየደረሱ ነው ተብሏል። ከእነዚህ መካከልም የማህበራዊ ሚዲያ በብዛትና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ተነግሯል። ይህንን እየተስፋፋ የመጣው በማህበራዊ ሚዲያ የአልኮል ማስታወቂያን በተቻለ መጠን ለመገደብ ታስቦ፤ የህግ ማዕቀፍ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚኝ በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ፍሬሰላም ዮሴፍ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ…
Read More
ብሔራዊ ሎተሪ 50 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ሎተሪ ይፋ አደረገ

ብሔራዊ ሎተሪ 50 ሚሊዮን ብር የሚያሸልም ሎተሪ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እንደገለፀው ይህ ዘመናዊ ሎተሪ ከወረቀት ሎተሪ በተጨማሪ በዲጅታል መላ በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብሏል። በዲጂታል ሎተሪ ለረጅም ዓመታት በመፋቅ እድለኛ የሚያደርጉት የፈጣን እና የቢንጎ ሎተሪዎችም በዲጅታል መንገድ እንደተካተቱ ተገልጿል።ከሀምሳ ሚሊዮን ብር ሽልማት አንስቶ በርካታ የጨዋታ አማራጮችን የቀረበበት  ሲሆን በስምንት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ይህንን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ ከተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር  እየሰራ መሆኑን ገልጿል። አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዲጅታል ሎተሪ በተጨማሪ በሃምሳ ሺህ ብር ሽልማት የከፈተውን የእድል በር ወደ ሃምሣ ሚሊየን ብር ከፍ ለማድረግ እንደበቃም ተናግሯል። ብሔራዊ ሎተሪ በየጊዜው አዳዲስ የሎተሪ እድኮችን ለደንበኞቹ ያስተዋወቀ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት አድማስ…
Read More
የገቢዎች ሚንስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ 649 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

የገቢዎች ሚንስቴር በዘጠኝ ወራት ውስጥ 649 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

ሚኒስቴሩ በተያዘው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 649 ቢሊዮን ብር ሰብስቤያለሁ ብሏል ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ 74 በመቶ ወይም የ279 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡ ከተሰበሰበው ገቢ 345.9 ቢሊየን ብሩ ከታክስ የተገኘ ሲሆን ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 307.2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገልጿል። ገቢው በመቶ ቢሊዮኖች ከአምናው ከፍ ያለበት ምክንያት ግን በሪፖርቱ አልተብራራም፡፡ በሌላ በኩል ህገ-ወጥ ንግድ ፣ ገቢን መደበቅ ፣ ግብይትን ያለ ደረሰኝ መከወን ፣ ግብር ስወራና ታክስ ማጭበርበር አሁንም ፈተና ሆነውብኛል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡ ተሰውሮብኝ ነበር ያለውን ገቢ ለማግኘትም በድንገተኛ ፍተሻ ፣ በሒሳብ ምርመራ ወይም ኦዲትና መሰል ስራዎች የህግ ማስከበር ስራ ሰርቻለሁ ብሏል፡፡ በዚህም 7 ሺህ 583 የሒሳብ…
Read More
የብሪክስ አባል ሀገራት 65 በመቶ ግብይታቸውን ከዶላር ውጭ ማድረጋቸው ተገለጸ

የብሪክስ አባል ሀገራት 65 በመቶ ግብይታቸውን ከዶላር ውጭ ማድረጋቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ አባል በሆነችው ብሪክስ የንግድ ልውውጥ ከዶላር እየራቀ 65 በመቶ በብሔራዊ ገንዘቦች እየተከናወነ ነው ተብሏል። የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያን ጨምሮ አባል የሆኑት የብሪክስ አገራት (ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች) በንግድ ልውውጣቸው ከአሜሪካ ዶላር እየራቁ ሲሆን ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ንግድ አሁን በአባል አገራቱ ብሔራዊ ገንዘቦች እየተከናወነ ነው። ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በብራዚል በተካሄደው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ በሰጡት መግለጫ ሲሆን፣ ይህ አዝማሚያ ቡድኑ በፋይናንስ ረገድ ያለውን ነፃነት ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል። ላቭሮቭ አክለውም "BRICS Pay" የተባለ ገለልተኛ የክፍያ ስርዓት ለመመስረት የሚደረጉ ውይይቶች እየተሻሻሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።…
Read More
ኢትዮጵያ የጣና ደሴት እና ገዳማትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ዘመቻ ጀመረች

ኢትዮጵያ የጣና ደሴት እና ገዳማትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ዘመቻ ጀመረች

የጣና ሀይቅ ደሴትና ገዳማት በአለም አቀፍ የቅርስ መዝገብ እንዲሰፍሩ የሚያስችለዉ ሰነድ ለዮኔስኮ ተልኳል። በአማራ ክልል የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  አስታውቋል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ እምቢአለ እንደተናገሩት በክልሉ የሚገኙ በርካታ የመስህብ ቦታዎች እንደመኖራቸው የጣና ሀይቅ እና አካባቢውን በዮኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ከዚህ ቀደም  የጣና ሀይቅ ደሴቶች በብዛ ህይወት ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ወቅት ይህ ስፍራ በአለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ በተዘጋጀዉ ሰነድ ዙሪያ ማስተካከያ መደረጉን ተናግረዋል። ሰነዱን አስመልክቶ አስተያየት የመስጠትና ተጨማሪ ግብዓቶችና ማስተካከያዎችን የማዘጋጀት ስራ ሲሰራ እንደቆየ የገለፁት…
Read More
የአውስትራሊያው የማዕድን አሳሽ አስካሪ ሜታልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

የአውስትራሊያው የማዕድን አሳሽ አስካሪ ሜታልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ

ዋና መቀመጫውን ፐርዝ አውስትራሊያ ያደረገው ግዙፍ የማዕድን አሳሽ አስካሪ ሜታልስ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ውስጥ አዲስ የኢንቨስትመንት ውል ፈጽሟል። አስካሪ ሜታልስ የተባለ የማዕድን አሳሽ ኩባንያ በአፍሪካ ያለውን የፍለጋ እንቅስቃሴውን ወደ ኢትዮጵያ በማስፋፋት ሪፍት ቫሊ ሜታልስ የተባለውን የግል ኩባንያ ሙሉ በሙሉ ለመግዛት ስምምነት ላይ መድረሱን በይፋ አስታውቋል። ሪፍት ቫሊ ሜታልስ በደቡባዊ ኢትዮጵያ በሚገኘው በአዶላ አካባቢ አምስት ትላልቅ የወርቅ ፕሮጀክቶች ባለቤት ሲሆን፣ ይህ ስምምነት አስካሪ ሜታልስ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙትን ሳካሮ፣ ሳካሮ ምዕራብ፣ ሌጋ ደምቢ ደቡብ፣ ሜጋዶ እና ዋዩ ቦዳ የተባሉትን 460 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ፕሮጀክቶች እንዲያገኝ አስችሎታል። ይህ ስምምነት አስካሪ ሜታልስ ከፍተኛ መጠን ያለው የወርቅና የመዳብ…
Read More