ዜና

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል የመንግስት ባለስልጣንን ለመግደል ሞከሩ

የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል የመንግስት ባለስልጣንን ለመግደል ሞከሩ

እንዲሁም ታጣቂዎቹ የላሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪን እንዳቆሰሉ ቢቢሲ ዘግቧል። ታጣቂዎች ተቆጣጥረውታል የተባለው አካባቢ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ከተማ እንደሸሹም ተገልጿል። ኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳንን ከምትጎራበታቸው ክልሎች አንዱ በሆነው ጋምቤላ ታጣቂዎች ጥቃት መፈጸም የጀመሩት ከትናንት በስቲያ ከረቡዕ ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ አንድ የላሬ ወረዳ ኃላፊ ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ "የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው የገቡት" ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ ያሉት የሱዳን ሕዝቦች ነጻነት እንቅስቃሴ/ተቃዋሚ (Sudan People's Liberation Movement In Opposition) ታጣቂዎች ናቸው። ታጣቂዎቹ የገቡት የኑዌር ብሔረሰብ ዞን ላሬ ወረዳ ስር በምትገኘው የድንበር አካባቢዋ ፓጋግ ቀበሌ እንደሆነ ምንጩ ገልጸዋል። ከሀገሪቱ መንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ ያሉት ታጣቂዎች ድንበሩን አቋርጠው የገቡት "ተኩስ ሲከፈትባቸው…
Read More
ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎች የቋሚ ንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

የውጭ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም የመሬት ባለይዞታ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው የአዋጅ ረቂቅ ተዘጋጅቷል፡፡ አዋጁ የተዘጋጀው “የዜጎችን የመሬት ይዞታ የማግኘትና የመጠቀም መብት በማያጣብብ መልኩ” እንደሆነ ተገልጿል። የውጭ ዜጎች ካፒታላቸውን “በኢትዮጵያ ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማበረታታት” የታለመ ነው የተባለለት ይህን የህግ ረቂቅ ለፓርላማ የመራው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ የአዋጅ ረቂቁን ጨምሮ በስድስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎች የመሬት እና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ህጋዊ አሰራር እንዲዘረጋ ከተደረገባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ ለኢትዮጵያውያን “የስራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ” ያለው በመሆኑ እንደሆነ ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እና…
Read More
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች በወሲብ ንግድ መሰማራታቸው ተገለጸ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች በወሲብ ንግድ መሰማራታቸው ተገለጸ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮን ለማሸነፍ ስላላስቻላቸው ማታ ማታ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ መኖራቸውን በጥናት መለየቱን የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሴት ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ትርፍራፊ ምግቦችን ይዘው ወደ ቤታቸው የሚገቡ እንዳሉም ፌደሬሽኑ ጠቁሟል፡፡ አምራች ስራተኛ፣ ምቹ ስራ ለወጣቶች እና ሴቶች በጨርቃ ጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ መፍጠር በሚል ርዕስ የፖሊሲ አቅጣጫ ጠቋሚ ጥናት ለማድረግ የማህበራት ጥናት መድረክ (Forum For Social Studies) በጠራው የሁለተኛ ዙር የባለድርሻ አካላት ወይይት ላይ የተገኙት የጨርቃ ጨርቅ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ ተስፋዬ አብዲሳ ‘’የሚከፈላቸው ደመወዝ ለኑሮ ስለማይበቃቸው ማታ ማታ ከሆቴሎች ተመላሽ ምግቦችን ይዘው የሚገቡ እንዳሉም በጥናት…
Read More
ኢትዮጵያ በሁሉም ወረዳዎች ኢንዱስትሪ የማቋቋም እቅድ እንዳላት ተገልጸ

ኢትዮጵያ በሁሉም ወረዳዎች ኢንዱስትሪ የማቋቋም እቅድ እንዳላት ተገልጸ

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ፤ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነግሯል፡፡ እቅዱ በገጠር ያሉ ዜጎች የሚፈልጓቸውን ምርቶች ለመግዛት ወደ ከተማ እንዳይጓዙ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡ በሀገሪቱ ያሉ ወረዳዎች በየአካቢያቸው እንደሚያገኙት የግብዓት ዓይነት፤ እያንዳንዳቸው እስከ 3 ኢንዱስትሪዎች እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል፡፡ በዚህም ባለፉት 9 ወራት 206 ኢንዱስትሪዎች በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች መቋቋማቸውን የጠቀሰው ተቋሙ፤ ቁጥራቸውን ለማሳደግ እቀጥላለሁ ብሏል፡፡ በገጠር አካባቢዎች ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት የአካባቢው ነዋሪዎች ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ፤ የስራ እድል በመፍጠር ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ይቀንሳልም ተብሏል፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ 151,000 ሰዎች በመካከለኛ እና በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ስራ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱልፈታ…
Read More
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ83 ሺህ በላይ  ሰዎች በካንሰር ምክንያት ይሞታሉ ተባለ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ83 ሺህ በላይ  ሰዎች በካንሰር ምክንያት ይሞታሉ ተባለ

በኢትዮጵያ  የካንሰር ታማሚዎች ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱት የህመሙ ደረጃ ሶስት እና አራት ከደረሰ በኋላ መሆኑ ተገልጿ። ይህንን ለማዳን ከባድ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑም በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ሌሊሳ አማኑኤል ተናግረዋል።  የካንሰር ህመም  ቀድሞ ማከም እና መከታተል ከተቻለ መዳን የሚቻል ህመም መሆኑን አማካሪው ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛ መምጣቱን እና በዓመት ከ83 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሰር በሽታ እንደሚያዙም አክለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት 19 ሚሊዮን ሰዎች በካንሰር የሚያዙ ሲሆን 10 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተነግሯል። ከእነዚህም መካካል 75 በመቶ የሚሆነው  ዝቅተኛ የሆነ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሀገራት ላይ የሚከሰት መሆኑ ተገልጿል ። በሌላ በኩል የህጻናት የካንሰር…
Read More
የለንደን ማራቶን በኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ

የለንደን ማራቶን በኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ

ዛሬ ፍጻሜውን ባገኘው የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን እና ኬንያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በ2025 በሴቶች ውድድር ትግስት አሰፋ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ በወንዶች ደግሞ ኬንያዊው ሴባስቲያን አሸንፏል። አትሌት ትግስት አሰፋ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን ( 2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች። ታሪካዊቷ ብሪታንያዊት የማራቶን ሯጭ ፓውላ ራድክሊፍ በሰጠችው አስተያየት አትሌት ትዕግስት አሰፋ ውድድሩን የጨረሰችበትን መንገድ አድንቃ ጀግና አትሌት ነሽ ብላታለች፡፡ አትሌት ትግስት አሰፋ ውድድሯን 2:15:50 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ማጠናቀቋን ተከትሎ በሴቶች ብቻ የአለም የማራቶን ሪከርድን (2:16:16 ) 2:15:50 በሆነ ሰዓት መስበር ችላለች። ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ስታጠናቅቅ በውድድሩ ስትጠበቅ የነበረችው ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አተናቃለች። በተመሳሳይ የወንዶች…
Read More
ኢትዮጵያ ለሱዳን የምትልከው ኤሌክትሪክ ሀይል 80 በመቶ ቀነሰ

ኢትዮጵያ ለሱዳን የምትልከው ኤሌክትሪክ ሀይል 80 በመቶ ቀነሰ

በሱዳን ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት፣ ኢትዮጵያ ወደ ሀገሪቱ የምትልከው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን በ80 ከመቶ ያህል መቀነሱን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል፡፡ የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የሱዳን የሃይል መሰረተ ልማት በጦርነቱ በመጎዳቱ የታቀደውን ያህል መጠን ሀይል መላክ አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡ አቶ ሞገስ መኮንን እንዳሉት “ከሱዳን ጋር የተደረገው ስምምነት እስከ 100 ሜጋዋት ድረስ ለመላክ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን በመጠን ደረጃ በጣም ቀንሷል፡፡ ከ10 እስከ 20 ሜጋዋት ድረስ ነው እየላክን ያለነው፡፡ ዝቅ ሲል እስከ 10 ሜጋዋት፣ ከፍ ሲል ደግሞ እስከ 20 ሜጋዋት ይሆናል የምንልከው፡፡ ይህ የሱዳን የኤሌክትሪክ ሃይል መሰረተልማት በጦርነት በመጎዳቱ የመጣ ችግር ነው፡፡ ግጭቱ በጣም ከፍተኛ በሆነ…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም የ10 ሚሊዮን አክስዮን መሸጡን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም የ10 ሚሊዮን አክስዮን መሸጡን አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ከ47 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ባለድርሻ መሆናቸውን ገልጿል። የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ሽያጭ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በማስጀመር የአክሲዮን ሽያጩን እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡ በመቀጠልም ውጤቱን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እና ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣንበማቅረብ እና በመገምገም በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የሽያጭ ቀነ-ገደቡን በማራዘም እስከ የካቲት7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ማለትም ለ121 ቀናት በዲጂታል መንገድ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት የተከናወነው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ ውጤት በየደረጃው በሚገኙየመንግስት አካላት ተገምግሞ እንዲሁም በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታይቶ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡ ከ47 ሺህ በላይ ዜጎችን በኢትዮ ቴሌኮም ውስጥ የባለቤትነት…
Read More
ሆላንድ ዴይሪ የሙዝ ጣዕም ያለው እርጎ ለገበያ አስተዋወቀ

ሆላንድ ዴይሪ የሙዝ ጣዕም ያለው እርጎ ለገበያ አስተዋወቀ

የሆላንድ ዴይሪ የወተት ምርት አዲስ የሙዝ ጣዕም ያለው እርጎ ለኢትዮጵያ  ገበያ ማቅረቡን ገልጿል። የሆላንድ ዴይሪ የሙዝ እርጎ አመጣጥ የኢትዮጵያውያን ሸማቾች ጣዕምን የሚያሟላ የወተት ተዋጽእዎችን ማቅረብ ላይ በማተኮር፣ የክሬም ይዘት ያለው ከተፈጥሯዊ  የሙዝ ፍሬ ጣፋጭነት ጋር በማዋሃድ የሀገሪቱን የወተት ምርታማነት መስፈርት በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱን ቀጥሏል ተብሏል። ይህ አዲስ የሙዝ እርጎ ምርት አሁን ያለውን የስትሮውበሪ (ኢንጆሪ) እና የማንጎ እርጎ አቀራረብ አይነት በሚገባ እንደሚያሟላም ኩባንያው አስታውቋል። ይህም የተቋሙን አቅርቦት በሌላ ከፍተኛ ጥራት ባለው ምርት በማሳደግ በሀገር ውስጥ ምርቱ በንቃት እንዲስፋፋ ያደርጋል ነው የተባለው። የሆላንድ ዴይሪ የወተት ተዋጽኦዎችን ለማቅረብ ከ4ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንስሳት አርቢዎች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል። ሆላንድ ዴይሪ የደች ቴክኖሎጂን…
Read More
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከእሁዱ የ2025 ለንደን ማራቶን ውድድር ውጪ መሆኑን አዘጋጆቹ ይፋ አድርገዋል። አትሌቲ ቀነኒሳ በቀለ በጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን ውድድር መሳተፍ እንደማይችል አስታውቋል። አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፌስቡክ ገጹ እንዳለው “በእሁዱ የለንደን ማራቶን ወደ ውድድር ለመመለስ ጓጉቼ ነበር ባለመሳካቱ በጣም ተበሳጭቻለሁ“ ብሏል። ከውድድሩ ውጪ የሆነው በጉዳት መሆኑን ያረጋገጠው ቀነኒሳ በውድድሩ ለሚካፈሉ አትሌቶች መልካም ምኞቱን ገልጿል። በለንደን ማራቶን ውድድር አንደኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ተወዳዳሪ 55 ሺህ ዶላር ሁለተኛ 33 ሺህ እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 22 ሺህ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ንጉስ የሆነው ቀነኒሳ በቀለ የፊታችን እሁድ በሚደረገው የለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ ይፋ አድርጓል ። ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የአሜሪካው አለምአቀፍ…
Read More