05
May
። ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በባንክ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የውጭ ባለሀብቶች አምስት የሚደርሱ የባንክ ፈቃድ ለመስጠት ማቀዷ ተገለጸ፡፡ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ የውጭ ባለሀብቶች የባንክ ፈቃድ እንደሚሰጥ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ይህም የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ አገልግሎት ለውጭ ተፎካካሪዎች ክፍት ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡ እስካሁን የባንኩ ዘርፍ ለውጭ አገራት መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ዝግ ሆኖ የቆየ ሲሆን፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት ውስጥ ግን ለውጭ አገራት ተፎካካሪዎች ክፍት እንደሚደረግ ነው የተገለጸው፡፡ በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ዘርፉም ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በጋራ የሚሰሩበት አማራጭ ሊኖር እንደሚችል በምክትል ገዥው በኩል ተጠቅሷል፡፡ የውጭ…